Logo
Getu Temesgen
"ልጃችን መማር ያለበት አዳሪ ትምህርት ቤት ነው!" ንጉሳዊያን

*ንጉሳዊያኑ ልጃቸውን ኢተን አዳሪ
ትምህርት ቤት አስገቡ!
#ethiopia | የእንግሊዝ የንጉሳዊያን አልጋ ወራሽ ልዑል ዊሊያም እና ባለቤታቸው ልዕልት ኬት ሚድልተን ታላቅ ልጃቸውን ልዑል ጆርጅ "ኢተን"በመባል የሚታወቀው የአዳሪ ትምህርት ቤት አስገብተዋል።

በዕለቱም ወላጆቹ ከልጃቸው ጎን በመገኘት የመጀመሪያ የትምህርት ቀኑን በደስታ አጅበውት ታይተዋል።

የንጉሣውያኑ ቤተሰብ ልጃቸው በአዳሪ ትምህርት ቤት ሥርዓት ውስጥ እንዲያልፍ መምረጣቸው በብዙዎች ዘንድ ትልቅ ትኩረትን ስቧል።

አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከወላጆቻቸው ርቀው በራሳቸው የመኖር ሰዓት የማክበር፣ ኃላፊነት የመውሰድ እና የዕለት ተዕለት ውሳኔዎችን በራሳቸው የመስጠት ልምድ እንዲያዳብሩ ያደርጋል።

የወደፊቱ የእንግሊዝ ንጉሥ የሚሆነው ልዑል ጆርጅ ገና በለጋ ዕድሜው ጠንካራ እና ራሱን የቻለ መሪ እንዲሆን ለማድረግ ታስቦ ነው ተብሏል።

ኢተን ኮሌጅ በርካታ የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትሮችን፣ የፖለቲካ መሪዎችን እና የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎችን ያፈራ ትምህርት ቤት በመሆኑ ልዑሉ የአመራር እና የትምህርት ጥራት ሥርዓት ውስጥ እንዲያልፍ ያደርገዋል ተብሏል።

ለልዑሉ የወደፊት የንጉሥነት ዘመን የሚመጥን ስነምግባሩ እና የአመራር ብቃት ለመገንባት የተደረገ ስትራቴጂያዊ እርምጃ መሆኑን ተነግሯል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ethiopia #getutemesgen #etoncollege #princegeorge #princewilliam #katemiddleton #royalfamily #boardingschool

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.