(ዘ-ሐበሻ ዜና) በአሜሪካ ሚኒሶታ ግዛት ነዋሪ የነበረችው እና ማንም ባላሰበው አሳዛኝ ሁኔታ ከሁለት ዓመት ህጻን ልጇ አጠገብ ሕይወቷ አልፎ የተገኘችው የ33 ዓመቷ ወጣት አዱት (ፍጹም) ሲሞን ማሉዋል (የክርስትና ስሟ ወለተ ሩፋኤል) ሥርዓተ ቀብር በዛሬው ዕለት እንደሚፈጸም የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ በሚኒሶታ አስታወቀ። ይህ ልብ የሚሰብር ድንገተኛ ህልፈት የአካባቢውን ማኅበረሰብ በከባድ ሀዘን ውስጥ የከተተ ሲሆን፣ የነፍስ ይማር ጸሎት እና የሽኝት መርሃ ግብሩ ዛሬ ማክሰኞ ጳጉሜን 3 ቀን 2018 ዓ.ም (ሴፕቴምበር 8 ቀን 2026) ይከናውናል።
በወጣው መርሀ ግብር ላይ ላይ እንደተመለከተው፣ የወጣቷ የጸሎተ ፍትሐት ሥርዓት ዛሬ ከጠዋቱ 11፡00 ኤኤም (11:00 AM) ጀምሮ በሚኒያፖሊስ ከተማ በሚገኘው ርዕሰ አድባራት ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ውስጥ ይከናወናል። ይህ የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ከተጠናቀቀ በኋላ፣ አስከሬኗ በሴንት ፖል ከተማ ወደሚገኘው ኦክላንድ መካነ መቃብር አቅንቶ ሥርዓተ ቀብሯ በክብር የሚፈጸም ይሆናል።
ከቀብር ሥርዓቱ ፍጻሜ በኋላ ሀዘንተኞች፣ ቤተሰቦች እና ወዳጅ ዘመዶች ለነፍስ ይማር እና ለጸበል ጻድቅ ሥርዓት በሚኒያፖሊስ ወደሚገኘው ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተመልሰው ይሰባሰባሉ። ፈጣሪ ለወጣቷ ነፍስ የዘላለም ዕረፍትን፣ ከጎኗ ለተገኘው የሁለት ዓመት ህጻን ልጇ እና ለመላው ቤተሰቧ ደግሞ መጽናናትን እንዲሰጥ እንመኛለን።

30 days ago