ሼር
ከቦምብ የተሰራው ልብ የሚነካ ሐውልት 😭
በእሲያ ጉብኝቴ ላኦስ የተባለችውን ሀገር ስጎበኝ ይህን ሐውልት አየሁት መጀመሪያ ስመለከተው ከተራ ቆርቆሮና ብረት የተሰራ የጥበብ ስራ መስሎኝ ነበር። ነገር ግን ጠጋ ብዬ ሳስተውልና የጀርባ ታሪኩን ስረዳ፣ ትኩረቴን ሳበው። ይህ ሀውልት የተሰራው የሰውን ህይወት ከሚቀጥፉ ትክክለኛ የከሸፉ የቦምብ እና የሚሳኤል ቅርፊቶች ነው! ታሪክ እንደሚነግረን፣ አሜሪካ በላኦስ ላይ ከ260 ሚሊዮን በላይ ቦምቦችን አዝንባለች። በዚህ አሰቃቂ የቦምብ ድብደባ ምክንያት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ተጎድተዋል፤ ህይወታቸውን አጥተዋል፣ አካል ጉዳተኛ ሆነዋል፣ ትውልድ ተመሰቃቅሏል።
ከእነዚህ የሞት እና የጥፋት መሳሪያዎች ስብርባሪ የተሰራው ይህ ሀውልት ከቦምብ ዝናብ እና ከጦርነት አውድማ ነፍሳቸውን ለማትረፍ የሚሸሹ እናትና ልጅን ያሳያል። እናትየው በአንደኛው እጇ የልጇን እጅ አጥብቃ ይዛ፣ በሌላኛው እጇ ደግሞ መጪውን አደጋ ለመከላከል ስትጥር ትታያለች።
እስካሁን በጎበኘኋቸው ሀገራት ሁሉ የተገነዘብኩት ትልቅ ሀቅ ቢኖር፣ ሁሉም የየራሳቸው የጦርነት ጠባሳና ታሪክ እንዳላቸው ነው። አንዳንዶቹ አሁንም ጦርነት ላይ ናቸው ታዋቂው ፈላስፋ በርትራንድ ራስል "ጦርነት ማን ትክክል እንደሆነ አይወስንም፤ ይልቁንስ ማን በህይወት እንደሚተርፍ እንጂ" እንዳለው፣ ይህ አውዳሚ ክስተት ማንንም አሸናፊ አያደርግም። በአጭሩ ታሪክን ብንፈትሽ የጦርነት አስከፊነት ያላንኳኳው እና ሰቆቃው ያላረፈበት የዓለም ጥግ ማግኘት ይከብዳል።
የሰላም ዋጋ እጅግ ውድ ነው። ይህንን ሀውልት እና ከጀርባው ያለውን ታሪክ ስትመለከቱ እናንተስ ምን ተሰማችሁ?
አቤል ብርሃኑ የወይኗ ልጅ
ከጉዞ ማስታወሻዬ ሴፕቴምበር / 2026 /
ላኦስ ቪየንቲየን ከተማ

1 month ago