የፀጥታ ተቋማት ዘመናዊ ቁመና እና ፅናት ለሀገር አለኝታነትና ሉዓላዊነት
*********************
በሀገረ-መንግሥት ግንባታ ሂደት ውስጥ የሉዓላዊነት መከበር፣ የዜጎች ደኅንነት እና የሀገር ዘላቂ መረጋጋት ዋነኛ መሠረቱ ጠንካራ፣ ጽኑ እና ዘመናዊ የፀጥታ ተቋማት ናቸው።
የፀጥታ ተቋሞቻችን ዘመናዊነት በታጠቁት መሳሪያ ብቻ ሳይሆን በከፍተኛ ዲስፕሊን፣ በሙያዊ ብቃት እና ማንኛውንም ስጋት በላቀ ስትራቴጂካዊ ዝግጁነት የመመከት አቅም ባለው ሠራዊት የሚገለጽ ነው።
ተቋማቱ ከፖለቲካዊ ወገንተኝነት ነፃ በመሆን ለሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱ እና ለሕዝብ ደኅንነት ብቻ ታማኝ በመሆን እውነተኛ የሕዝብ አገልጋይነታቸውን አስመስክረዋል።
ዓለም በፈጣን የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በሳይበር እና በውስብስብ ጂኦ-ፖለቲካዊ ለውጦች ውስጥ በምትገኝበት በዚህ ወቅት፣ ተቋሞቻችን በሳይበር ደኅንነት፣ በዘመናዊ የመረጃ ፍሰት እና በላቁ የመከላከያ ቴክኖሎጂዎች በመታገዝ ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶችን አስቀድሞ የማክሸፍና የመከላከል አቅማቸውን በከፍተኛ ደረጃ አሳድገዋል።
የሀገራችንን ዳር ድንበር አስከብሮ የሀገርን ክብር እና ነፃነት ለማስጠበቅ በሚደረግ እያንዳንዱ እርምጃ ውስጥ የጀግኖቻችን ውድ ህይወት ተከፍሎበታል።
ይህ የተከፈለው መስዋዕትነት ለነገው ትውልድ የምትሻገር የተረጋጋች፣ የጸናች እና የተከበረች ኢትዮጵያን የማስረከብ ታላቅ ታሪካዊ አደራ ነው።
ጳጉሜን 3 የምናከብረው የጽናት ቀን ሀገርን በጽኑ መሠረት ላይ ለማቆም ያለመታከት የሚተጉ፣ ለሀገር ፍቅር እና ለሕዝብ ሰላም ሲሉ የእናት ሀገር ጥሪን አክብረው በየግንባሩ የቆሙ የፀጥታ አካላትን ውሎ፣ ጽናት እና ከፍተኛ የሀገር ፍቅር የምናስብበት ታላቅ ዕለት ነው።
በዚሁ የጽናት ቀን ለሀገር ፍቅር፣ ለሉዓላዊነት እና ለሕዝብ ሰላም ሲሉ ህይወታቸውን አሳልፈው የሰጡ የጀግኖቻችንን መስዋዕትነት ማሰብ፣ ማክበር እና በሥራ ላይ ያሉ የፀጥታ አካላትን ሞራል መገንባት የሁላችንም የዜግነት ግዴታ ነው።
በአድማሱ አራጋው
#ebc #dayofresilience #nationalsecurity #ethiopiandefense #sovereigntyandpeace #ethiopiarising

1 month ago