(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ ልዑካን ስቲቭ ዊትኮፍ እና ጃሬድ ኩሽነር በዩክሬን ባደረጉት ጉብኝት ምክንያት ለሦስት ቀናት ቆሞ የነበረውን ጥቃት ሩሲያ ዳግም በመጀመሯ፣ ማክሰኞ ንጋት ላይ በዋና ከተማዋ ኪየቭ ከባድ ፍንዳታዎች መሰማታቸው ተዘገበ።
በስፍራው የሚገኝ የሲኤንኤን ዘጋቢ እንዳረጋገጠው፣ ንገተኛው ፍንዳታ የተሰማው በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ሌሊት 9፡30 (3:30 a.m.) ገደማ ነው። የኪየቭ ከተማ ባለስልጣናት ወደ ከተማዋ የባሊስቲክ ሚሳኤሎች መተኮሳቸውን በማረጋገጥ፣ በሁለት ወረዳዎች በሚገኙ የመኖሪያ ሕንፃዎች ላይ ጉዳት መድረሱን አመልክተዋል።
ባለስልጣናቱ በቴሌግራም ገጻቸው ባስተላለፉት አስቸኳይ መልእክት፤ "የአየር ጥቃት ማስጠንቀቂያው እስኪነሳ ድረስ እባካችሁ በመጠለያ ስፍራዎች ውስጥ ቆዩ" ሲሉ ለነዋሪዎች ጥብቅ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል።
ዋሽንግተን በዩክሬን ያለውን ጦርነት ለማስቆም የጀመረችውን አዲስ የሰላም ጥረት ተከትሎ፣ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አማች ጃሬድ ኩሽነር እና ስቲቭ ዊትኮፍ እሁድ ዕለት በኪየቭ ከዩክሬን ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ተወያይተዋል። ልዑካኑ ይህንን ጉብኝት ያደረጉት፣ በሞስኮ ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር ጥልቅ እና ሰፊ ምክክር ባደረጉ ማግስት መሆኑ ይታወሳል።

1 month ago