''የአደይ አበባ ምንጣፍ..."
መስከረም ሲጠባ፣ ሰማዩ ከዳመናው ተላቆ ፊቱን ሲያጠራ፣ ምድሪቱ በአደይ አበባ ወርቃማ ቀሚስ ስታጌጥ፤ በኢትዮጵያውያን ልብ ውስጥ አዲስ ተስፋ ይፈነጥቃል።
በባህላችን አዲስ ዓመት የዘመን መለወጫ ብቻ ሳይሆን፣ የይቅርታ፣ የእርቅ እና የዕድሳት ምዕራፍ ነው። "ያምናውን በአምና ትተን፣ አዲሱን በደስታ እንቀበል" እንደሚባለው፣ የቆየውን ቂምና ቁርሾ አሮጌው ዓመት ይዞት እንዲሄድ በማድረግ፣ አዲሱን ዘመን በንጹሕ ልብ የምንቀበልበት የብሩህ ተስፋ መግለጫ ነው። ይህ የተፈጥሮ ዑደት እና የአዲስ ዓመት ብርሃን፣ ዛሬ ላይ ሀገራችን ከደረሰችበት ሁለንተናዊ የከፍታ ምዕራፍ ጋር በጥልቅ ይስተጋባል።
እናም፣ ምድር በክረምት ዝናብ ታጥባ፣ አረንጓዴ ምንጣፏን ዘርግታ በቢጫው አደይ አበባ ስትደምቅ፣ በተፈጥሮ ላይ የሚታየው ይህ መታደስ ለሀገራችን የፖለቲካዊ ዕድሳት ተምሳሌት ጭምር ነው።
ልክ እንደ አደይ አበባው መፈካት ሁሉ፣ ኢትዮጵያም ከረጅም የፖለቲካ ክረምትና ስብራት በኋላ ፊቷን ወደ መስከረም ብርሃን ሀገራዊ ምክክሯን አሳክታ ተመልሳለች።
ምድሪቱ በአደይ አበባ እንደምታጌጠው ሁሉ፣ የፖለቲካ ምኅዳራችንም በውይይት፣ በመቻቻል እና በጋራ መግባባት ማበብ ጀምሯል። ይህ ሀገራዊ ምክክር የትናንቱን ቁስል አድርቀን የነገውን ተስፋ የምንዘራበት የፈውስ ጉዞ ነው ። ክረምቱ የቱንም ያህል ከባድ ቢሆን መስከረምን እንደማያስቀር ሁሉ፣ የፖለቲካ ፈተናዎቻችንም በሕዝቦች የጋራ ውይይትና መግባባት ተፈትተው ብሩህ ዘመን መቷል።
ደግሞ ...
ልክ የፖለቲካ ምኅዳራችን በሀገራዊ ምክክሩ አዲስ ተስፋ እንደፈነጠቀ ሁሉ፣ የኢኮኖሚውም መስክ ከክረምቱ ፈተና ወጥቶ የፍሬ ዘመኑን ማብሰር ጀምሯል። ይህ የዕድሳት መንፈስ በጉባ ብስራት ግዙፍ ፕሮጀክቶች የልማት ዜና ታጅቦ መምጣቱ አዲሱን ዘመን ይበልጥ ልዩ ያደርገዋል።
ክረምት የዘር፣ የድካም፣ የጭቃ እና የፈተና ጊዜ ነው፤ መስከረም ደግሞ የፍሬ፣ የብርሃንና የስኬት መገለጫ ነው። ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ያሳለፈቻቸው መዋቅራዊ ማነቆዎች ልክ እንደ ክረምት የትግል ጊዜ ነበሩ። አሁን ግን ሀገሪቱ እየተገበረች ያለው የብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ የፋይናንስ ማነቆዎችን በመፍታት እና ዲፕሎማሲያዊ ጫናዎችን በመቋቋም ኢትዮጵያ እንደምታከናውን በተግባር ወዳጅም ጠላትም በአይኑ አረጋግጧል።
ይህ የማከናወን አቅም በጉባ ብስራቶች በኩል በተጨባጭ የሚታይ ሲሆን፣ አገሪቱ በኃይል፣ በኢንዱስትሪ፣ በአቪዬሽን፣ በማዕድንና በከተማ ልማት ዘርፍ አዲስ የታሪክ ምዕራፍ ከፍታለች ።
የቢሾፍቱ አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ በዓመት ከ110 ሚሊየን በላይ መንገደኞችን ለማስተናገድ የተነደፈው ፕሮጀክት፣ አገሪቱን የአፍሪካ ዋና የትራንስፖርትና የሎጂስቲክስ መገናኛ ኮሪደር በማድረግ የንግድ የበላይነታችንን ሲያስቀጥል ፤ የወደፊት የኃይል ፍላጎትን በዘላቂነት ለማረጋገጥ የተጀመረው የኒውክሌር ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ እንዲሁም በጎዴ እየተገነባ ያለው የተፈጥሮ ጋዝ ፋብሪካ ስኬት ኢትዮጵያን ወደ ላቀ የኢንዱስትሪ ምዕራፍ ያሸጋግራታል።
የግብርና ምርታማነትን የሚያረጋግጠው ግዙፍ የማዳበሪያ ፋብሪካ እና የውጭ ምንዛሪ ጫናን የሚያቃልለው የነዳጅ ማጣሪያ ፕሮጀክት፣ አገሪቱን ከውጭ ጥገኝነት የሚያላቅቁ ስትራቴጂካዊ ርምጃዎች ናቸው።
ከቀናት በፊት በተግባር እንደ አዲስ አመት ስጦታ ገቢርነቱ የተሰማው 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ቤቶችን ለመገንባት የተጀመረው ፕሮጀክት ፣ የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ከማሻሻሉም ባሻገር በቴክኖሎጂ የታገዘ ሰፊ የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር እርግጥ ነው ።
እነዚህ እርስ በርስ የተሰናሰኑ ግዙፍ የልማት ርምጃዎች በአጋጣሚ የመጡ ሳይሆኑ፣ ኢትዮጵያ በራሷ የመደመር መንገድ እና በረጅም ጊዜ አርቆ አሳቢነት የተመዘገቡ ድሎች ናቸው። የመደመር ጽንሰ-ሐሳብ ኢትዮጵያውያን ልዩነቶቻቸውን ወደ ጎን ትተው በሀገራዊ ምክክሩ እንዲፈወሱ ከማድረግ ባለፈ፤ የውስጥ አቅምን አጠናክሮ የውጭ ተግዳሮቶችን የመመከት አቅማችንን በተግባር ያረጋገጠ መሠረት ነው።
በቢሾፍቱ አውሮፕላን ማረፊያ ዓለምን ስናስተናግድ፣ በኒውክሌርና በተፈጥሮ ጋዝ ፋብሪካው ኃይላችንን ስናጎለብት፤ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የዲፕሎማሲ መድረክ ላይ አንገቷን ቀና አድርጋ ትራመዳለች። ይህም ብሔራዊ ጥቅሟን በክብር የምታስጠብቅበት የከፍታ ዘመን ማሳያ ነው።
ከተፈጥሮ መታደስ እስከ ፖለቲካዊ እርቅ፣ ከሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እስከ ግዙፍ የጉባ ብስራት ፕሮጀክቶች ድረስ የምናየው እውነት አንድ ነው፤ ኢትዮጵያ የብልጽግና እና የኢኮኖሚ ነፃነት ታሪካዊ መሠረቷን በጽኑ ጥላለች።
አዲሱ ዓመት ልክ እንደ ፈካው የአደይ አበባ፣ እነዚህን ግዙፍ የልማት ፕሮጀክቶች አፍክተን የድካማችንን ፍሬ የምንበላበት ዘመን ይሆናል። እንግዲህ የትናንቱን የክረምት ፈተና፣ ድህነት እና መከፋፈል ከኋላችን ትተን፤ በአዲሱ ዓመት አንድነታችንን አጠናክረን ወደ ብልጽግናው ማማ በአደይ አበባ ምንጣፍ እንረማመድ።
በኃይለኢየሱስ መኮንን

1 month ago