Logo
Getu Temesgen
ዳዊት ፅጌ ለአድናቂዎቹ ትልቅ ምስራች አብስሯል
#ethiopia | ዳዊት ፅጌ “የኔ ዜማ” የተሰኘውን የመጀመሪያ አልበሙን ለሙዚቃ አፍቃሪዎች ካበረከተ ከረጅም ዓመታት በኋላ፣ ሁለተኛ አልበሙን ለማቅረብ መዘጋጀቱን አስታውቋል።

“የኔ ዜማ” በወቅቱ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኘ ሲሆን፣ የዳዊት ፅጌን ልዩ የድምፅ ቀለምና የዜማ አቀራረብ ዘይቤ በጉልህ ያሳየ ሥራ ነበር።

በአራዳ ሙቭመንት በተዘጋጀው የዘመን መለወጫ — እንቁጣጣሽ ታላቅ ኮንሰርት ላይ ዳዊት ፅጌ በመድረክ በመቅረብ ተወዳጅ ሥራዎቹን ካቀረበ በኋላ፣ ሁለተኛ አልበሙን ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቁን ይፋ አድርጓል።

ድምፃዊው አልበሙ በ2019 ዓ.ም. መጀመሪያ ላይ ተጠናቆ ለህዝብ እንደሚቀርብ መግለጹ የሙዚቃ አፍቃሪዎችን በጉጉት እንዲጠብቁት አድርጓል።

ከመጀመሪያው አልበም በኋላ የቆየው የስድስት ዓመታት ጊዜ በአድናቂዎቹ ዘንድ ትልቅ የሙዚቃ ጥማት ፈጥሯል። አሁን ግን የዳዊት ፅጌ ሁለተኛ አልበም መምጣት የብዙዎችን ጉጉት እንደገና ቀስቅሷል።

እስከዳር ይኩን አምላክ! 🙏
#ዳዊትፅጌ #የኔዜማ #አዲስአልበም #እንቁጣጣሽ #አራዳሙቭመንት #ethiopianmusic #dawittsige

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.