Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) ታይላንድ የአዲስ አበባ ኤምባሲዋን ከ45 አመት በኋላ ድጋሚ ለመክፈት ወሰነች፡፡ ታይላንድ በአዲስ አበባ ኤምባሲዋን መልሳ ለመክፈት ዝግጅት እያደረገች መሆኑን አስታወቀች፡፡ ይህንን ያስታወቁት የአገሪቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሲሀሳክ ፉዋንግኬትኪው ሰሞኑን በኢትዮጵያ ይፋዊ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ነው፡፡ ታይላንድ እ.ኤ.አ በ1964 በኢትዮጵያ ኤምባሲ ከፍታ የነበረ ሲሆን ይሁንና እ.ኤ.አ በ1981 በአገሪቱ ውስጥ የነበረውን አለመረጋጋት ተከትሎ ዲፕሎማቶቿን አስወጥታ ኤምባሲውን ዘግታለች፡፡

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የሚያስተባብረው በኬንያ የሚገኘው የአገሪቱ ኤምባሲ ነበር፡፡ ይሁንና ከአራት አስርት አመታት በኋላ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ የታይ ዲፕሎማሲ ህልውና ሊመለስ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አስታውቀዋል፡፡ ታይላንድ የአዲስ አበባ ኤምባሲዋን የምትከፍተው ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ከማሰብም በላይ ከተማዋ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ በመሆኗ ከአፍሪካ ጋር ያላትን ትስስር ለማሳደግ ያለመም ነው፡፡

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.