(ዘ-ሐበሻ ዜና) ከሚያዚያ 2015 ጀምሮ በከባድ የርስበርስ ጦርነት ውስጥ ለምትገኘው ሱዳን፣ በራሳቸው በሱዳናውያን የሀገር ሽማግሌዎች አሰተባባሪነት በሀገሪቱ ውስጥ ሊካሄድ የታሰበውን "የሱዳን-ሱዳን" አገራዊ የምክክር እና የውይይት ማዕቀፍ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን በደስታ እንደሚቀበለው አስታወቀ።
የህብረቱ ኮሚሽን አመራር ባወጣው መግለጫ፣ ይህ ትልቅ ሃላፊነት የሚጠይቅ የፖለቲካ ሂደት ስኬታማ እንዲሆን የውይይቱ መድረክ በሱዳናውያን እውነተኛ ባለቤትነትና መሪነት ላይ የተመሰረተ መሆን እንዳለበት አሳስቧል። በተጨማሪም ሂደቱ ሁሉንም የሱዳን የሲቪል፣ የፖለቲካ እና የሲቪክ ማህበረሰብ ተወካዮችን ያካተተ (አካታች) ሊሆን እንደሚገባው ህብረቱ አጽንኦት ሰጥቷል።
የዚህ አዲስ የውይይት ማዕቀፍ ዋነኛ ግብ፤ ህጋዊ በሆነ የሲቪል ተቋማት የምትመራ፣ አንድ ወጥ የሆነ ብሔራዊ የጸጥታ መዋቅር (ያላት፣ እንዲሁም ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ልዩነቶቿን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያስችል ጠንካራ ስርዓት ያላት የተባበረች እና ሉዓላዊት ሱዳንን መፍጠር መሆኑ ተገልጿል።
ይህ በሱዳናውያን ባለድርሻ አካላት የሚመራው ተነሳሽነት፣ የአፍሪካ ህብረትን የሰላም ፍኖተ-ካርታ እና የ'ባለ አምስትዮሹን ስብስብ' ስትራቴጂካዊ አካሄድ ይበልጥ የሚያጠናክር ትክክለኛ እርምጃ መሆኑን ህብረቱ አስገንዝቧል።

1 month ago