ከታሪፍ በላይ የሚያስከፍሉ አሽከርካሪዎች የአምስት ሺህ ብር የገንዘብ ቅጣት ይጣልባቸዋል
#ethiopia | በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች ዘንድ የሚታየውን ያልተገባ የታሪፍ ጭማሪ እና የመስመር ማሳጠር ችግር ለመግታት ጥብቅ የቁጥጥር እርምጃ መውሰድ መጀመሩን የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ።
የቢሮው የኦፕሬሽን ዘርፍ ምክትል ሃላፊ አቶ ዳኛቸው ሽፈራው ለኢትዮ ኤፍኤም እንደገለጹት፣ ባለፈው የበጀት ዓመት ከተለያዩ የትራፊክ ጥፋቶች ጋር ተያይዞ ከ120 ሺህ በሚበልጡ አሽከርካሪዎች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ ተወስዷል።
ከእነዚህም መካከል 25 በመቶ ያህሉ ከተደነገገው ታሪፍ በላይ በማስከፈል በህዝብ ላይ እንግልት ሲያደርሱ የተገኙ ናቸው።
የከተማው ነዋሪ መሰል ህገወጥ ድርጊቶች ሲያጋጥሙት ዝምታን ከመምረጥ ይልቅ የተሽከርካሪውን የታርጋ ቁጥር በመያዝ በ9417 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ መስጠት እንደሚችል ቢሮው ጠቁሟል።
ከዚህ በኋላ ያለአግባብ የታሪፍ ጭማሪ በሚያደርጉ አሽከርካሪዎች ላይ የ5 ሺህ ብር ቅጣት የሚጣል ሲሆን፣ ድርጊቱን ደጋግመው በሚፈፅሙት ላይ ደግሞ እስከ ሙሉ ስራ ማገድ የሚደርስ የጠነከረ እርምጃ እንደሚወሰድ ተመል hisቷል።
#addisababatransport #transportbureau #tariffincrease #publictransport #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

1 month ago