Logo
Getu Temesgen
በኢትዮጵያ የሐምሌ ወር የኑሮ ውድነት መጠን ጨመረ
#ethiopia | የስታትስቲክስ አገልግሎት ይፋ ባደረገው መረጃ መሠረት በሐምሌ ወር በሀገሪቱ የታየው አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ወደ 15.3 በመቶ ከፍ ብሏል።

ይህም ከዚህ ቀደሙ የ13.9 በመቶ ምጣኔ ጋር ሲነጻጸር ጭማሪ ያሳየ ሲሆን የምግብ ነክ ቁሳቁሶች ግሽበትም በተመሳሳይ ከ15.1 በመቶ ወደ 15.7 በመቶ አድጓል።

ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶችና አገልግሎቶች የዋጋ መጠን እንዲሁ ከ11.2 በመቶ ወደ 14.8 በመቶ አሻቅቧል።

በዚህ የዋጋ ጭማሪ ውስጥ የስጋ ምርቶች በ21.6 በመቶ፣ የፈሳሽ ዘይት በ20.3 በመቶ እንዲሁም የፍራፍሬ ዓይነቶች በ19.2 በመቶ ከፍተኛውን የዋጋ እድገት አስመዝግበዋል።
#ኢትዮጵያ #የዋጋግሽበት #ኢኮኖሚ #የምግብዋጋ #የስታትስቲክስአገልግሎት #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

1 month ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.