በ12ኛ ክፍል ሀገራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ ተማሪዎች መካከል በ2ኛ ደረጃ የተቀመጠችው የሕዳሴ ዘመኑ ስኬት
#ethiopia | በአማራ ክልል አዊ ብሔረሰብ አስተዳደር እንጅባራ በሚገኘው የአገው ምድር ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተማረችው ሕዳሴ ዘመኑ፣ በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና 583 በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ ሁለተኛውን ከፍተኛ ውጤት አስመዝግባለች።
በትምህርት ቤቷ ቤተ መጽሐፍት በስሟ የተሰየመላት ይህች ብልህ ተማሪ፣ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ ሁለተኛውን ከፍተኛ ውጤት ስትይዝ በሴቶች ደግሞ አንደኛ በመሆን አጠናቅቃለች።
ተማሪ ሕዳሴ ያስመዘገበችው ይህ የላቀ ውጤት ከፍተኛ ደስታ እንደፈጠረላት ገልጻለች። ለፈተናው ከመጀመሪያው ጀምሮ ልዩ ትኩረት በመስጠትና በቂ ዝግጅት በማድረግ የልፋቷን ውጤት ለማየት መበቃቷንም ተናግራለች።
በቀጣይ በትምህርት ሕይወቷ በኮምፒውተር ሳይንስ ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ ሙያ ተሰማርታ ሀገሯን ማገልገል እንደምትፈልግ ገልጻለች።
የሕዳሴ አባት መምህር ዘመኑ ምህረት (ዶክተር) በበኩላቸው፣ የልጃቸው የላቀ ውጤት እና ስኬት እጅግ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።
#አገውምድር #ትምህርት #12ኛክፍል #ፈተና #እንጅባራ #አማራ ክልል #አዊ #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

2 months ago