የገጠር ኮሪደር ፣ ለማህበረ ኢኮኖሚያዊ ሽግግር
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 18፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ የሚኖረው በገጠር ነው።
ይሁን እንጂ፣ ይህ ከፍተኛ ቁጥር ያለው አምራች ኃይል ለዘመናት በተበታተነና ባህላዊ በሆነ የአኗኗር ዘይቤ ውስጥ ለመኖር ተገዷል።
ይህም ሁኔታ እንደ ጤና፣ ትምህርት፣ ንጹሕ ውኃ እና ኤሌክትሪክ ያሉ መሠረታዊ የመንግሥት አገልግሎቶችን ተደራሽ ማድረግን እጅግ ፈታኝ አድርጎት ቆይቷል።
በተጨማሪም፣ አብዛኛው የገጠር ማኅበረሰብ ከእንስሳት ጋር አብሮ ለመኖር ከመገደዱ ባሻገር፣ የሚጠቀመው ማገዶ ለአካባቢ ብክለትና ለከባድ የመተንፈሻ አካላት ሕመም ሲዳርገው ቆይቷል።
ይህን ሥር የሰደደ ዘመናዊ አገልግሎቶች የማግኘት ችግር ለመቅረፍ፣ የመደመር መንግሥት መጀመሪያ በትልልቅ ከተሞች ላይ ትኩረት በማድረግ አጠቃላይ ገጽታቸውን የሚያድስና ዘመናዊ አደረጃጀትን የሚያጎናጽፍ የከተማ ኮሪደር ልማትን በአዲስ አበባና ሌሎች በርካታ ከተሞች ተግባራዊ አድርጓል።
ሆኖም የዜጎችን ሕይወት በተሟላ መልኩ ለመቀየር እና ሁለንተናዊ ብልፅግናን ለማረጋገጥ የከተማ ኮሪደር ልማት ብቻውን በቂ ባለመሆኑ፣ በከተሞች የታየውን አመርቂ ውጤት ወደ ገጠሩ ማሸጋገር አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።
በዚህም መሠረት በግንቦት ወር 2017 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) የአርሶ አደሩንና የአርብቶ አደሩን ሕይወት በመሠረታዊነት የሚለውጥ ሞዴል የገጠር መንደሮች ግንባታ ወይም «የገጠር ኮሪደር ልማት»ን ይፋ አድርገዋል።
የዚህ ሀገራዊ ውጥን ዋና ዓላማ አርሶ አደሩን ከጭስና ከጤና እንክብካቤ እጥረት በማላቀቅ፣ እንደ ሶላርና ባዮጋዝ ያሉ አኗኗርን የሚያቀልሉ አረንጓዴ ቴክኖሎጂዎችንና ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶችን ተደራሽ ማድረግ ነው።
እንዲሁም የተበታተኑ ሰፈሮችን በሞዴል መንደሮች በማደራጀት የትምህርት፣ የጤና፣ የመስኖ እና የንጹሕ ውኃ አቅርቦቶችን ማመቻቸትና የገጠሩን ምርታማነት ከገበያ ጋር በማገናኘት ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገብን ታሳቢ ያደረገም ነው።
በከተማ ደረጃ ያሉትን አገልግሎቶች በገጠር ማኅበረሰብ ዘንድ በማቅረብ ከገጠር ወደ ከተማ የሚደረግ ፍልሰትን መቀነስም ሌላኛው ዓላማ ነው።
በአሁኑ ወቅት ይህ ጥረት በተለያዩ ክልሎች በተጨባጭ ወደ ሥራ ተተርጉሟል። በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል «ሐማሳ ሞዴል መንደር» የመስኖ ልማትና ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶችን አጣጥሞ የያዘ ሰፈር ተገንብቷል።
በሲዳማ ክልል «ማጪሾ ቀበሌ» አርሶ አደሩን ከጭስ ያላቀቀ ጽዱ መንደር ሲፈጠር፣ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ «ጉራፈርዳ ወረዳ» ደግሞ አቅመ ደካሞችንና አርሶ አደሮችን ያካተቱ ሞዴል ቤቶች ተገንብተዋል።
በተጨማሪም በአማራ ክልል በጎንደር ዙሪያ «ሳይና ሳቢያ ቀበሌ» እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በወንጪና ጅማ አካባቢዎች ተመሳሳይ የገጠር ኮሪደር ልማቶች በተስፋፋ ሁኔታ እየተከናወኑ ይገኛሉ።
በገጠር የሚገነቡ ሞዴል መንደሮቹ ቀላል ወጪ በሚጠይቁና በአካባቢው በሚገኙ ግብዓቶች የሚገነቡ ከመሆናቸውም በላይ አርሶ አደሩ ጤናማ እና ክብር ያለውን ህይወት እንዲኖር የሚያስችሉ በመሆናቸው፤ የተስተካከለ ኑሮን እና ከተሜነትን ወደ ገጠር ያመጣል ።
በአጠቃላይ፣ የገጠር ኮሪደር ልማት የገጠሩን ማኅበረሰብ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መዋቅር በመቀየር፣ ኢትዮጵያ የያዘችውን ሁለንተናዊና አቃፊ የብልፅግና ጉዞ ለማፋጠን የታለመ መሠረታዊ ሀገራዊ ሽግግር ነው።
በቴዎድሮስ ሳህለ

1 month ago