(ዘ-ሐበሻ ዜና) በቅርቡ ጅቡቲ የባብ ኤል-መንደብን ባህረ ሰላጤ ደህንነት ለማስጠበቅ ዓለም አቀፍ ኃይሎች እና የባህር መስመሩ ዋነኛ ተጠቃሚዎች ኃላፊነት እንዲጋሩ ያቀረበችው ጥሪ፣ በአፍሪካ ቀንድ የጂኦ-ፖለቲካዊ ትኩረት አቅጣጫን የሚቀይር ክስተት መሆኑን አዲስ ጥናት አመላከተ።
ሳሚያ መሐመድ የተባሉ ተመራማሪ ዛሬ ባወጡት ትንታኔ ይህ የጅቡቲ ጥሪ ሀገሪቱ ባህረ ሰላጤውን ለብቻዋ የመጠበቅ አቅም እንደሌላት በይፋ ያመነችበትና በስፍራው የሚከሰት አደጋ ከሆርሙዝ የባህር መስመር መዘጋት እጅግ ሊከፋ እንደሚችል የተሰጠ ማስጠንቀቂያ መሆኑን አስነብበዋል።
በኢትዮጵያ እና በጅቡቲ መካከል ያለው ግንኙነት መዋቅራዊ አለመመጣጠን በግልጽ የሚታይበት ነው። የኢትዮጵያ የውጭ ንግድ ከሞላ ጎደል በጅቡቲ ወደቦች ላይ የተንጠለጠለ በመሆኑ፣ ለኢትዮጵያ ጉዳዩ የኢኮኖሚ ብቻ ሳይሆን የህልውና ጉዳይ ነው። በባብ ኤል-መንደብ ላይ የሚፈጠር ማንኛውም የጸጥታ መስተጓጎል የኢትዮጵያን የገቢ ንግድ በማስተጓጎል የውጭ ምንዛሬን እና ፖለቲካዊ መረጋጋትን ክፉኛ ሊያናጋው ይችላል።
በሌላ በኩል የጅቡቲ የኢኮኖሚ ሞዴል በኢትዮጵያ የጭነት መጠን ላይ የተመሰረተ ነው። ሆኖም አደጋው ሲመዘን ኢትዮጵያ ከፍተኛ የህልውና ሥጋት ሲያንዣብብባት፣ ጅቡቲ ግን የሚያጋጥማት የሥራ ማስኬጃ ) ሥጋት ብቻ ነው።
ጅቡቲ እስካሁን የባህር በር ሉዓላዊነቷን በመጠቀም የተለያዩ የውጭ ሀገራት ወታደራዊ የጦር ሰፈሮችን በማስተናገድ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ጥቅም ስታገኝ ቆይታለች። በዚሁ ልክ ኢትዮጵያ የራሷ የሆነ የባህር ኮሪደር ወይም የባህር ኃይል ጦር ሰፈር በጅቡቲ ለማቋቋም ስታቀርብ የነበረውን ጥያቄ ጅቡቲ በተደጋጋሚ ስትገፋው ኖራለች። ይሁን እንጂ ጅቡቲ አሁን ያቀረበችው "የጋራ ኃላፊነት" ጥሪ፣ የነበረው ነባር የአንድዮሽ የጸጥታ አደረጃጀት አቅሙ ማለቁን የሚያሳይ ማረጋገጫ ነው።
ጥናቱ እንደሚሞግተው ኢትዮጵያ ይህንን የጅቡቲ የትብብር ጥሪ እንደ ወሳኝ ዕድል በመጠቀም፣ ኃላፊነትን በግዴታ የመጋራት ስትራቴጂ መከተል አለባት። ኢትዮጵያ ካለባት አንገብጋቢ የህልውና አደጋ አንጻር መረጃ በመለዋወጥ፣ በጋራ የጸጥታ ጥበቃ እና አቅም ግንባታ ላይ ተመጣጣኝ ሚና የሚሰጣት መደበኛ የጋራ የጸጥታ ማዕቀፍ እንዲቋቋም በአፋጣኝ መጠየቅ ይኖርባታል።
አማራጭ ወደቦችን የማልማቱ ጉዳይ ገና ዓመታትን የሚጠይቅ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ አሁን ላይ የህልውናዋ መሠረት የሆነውን የባህር መስመር ደህንነት በዝምታ መመልከት አትችልም። ተመራማሪዋ ትንታኔያቸውን ሲያጠቃልሉ "አሮጌው አሰራር እያከተመ ነው፤ አዲሱ አሰራር ደግሞ ኢትዮጵያ የራሷን ሚና እንድትወስን እና ተቋማዊ ተጽዕኖዋን እንድታሳድግ ያስገድዳታል" ሲሉ አሳስበዋል።

2 months ago