Logo
Getu Temesgen
"እሳት በእኔ ላይ ምንም አይነት የበላይነት የለውም!"
#ethiopia | በ6 ዓመቱ የሰውነቱ 73 በመቶ ክፍል በእሳት የተቃጠለው ህጻን ከዓመታት በኋላ የእሳት አጥፊ ባለሙያ ሆኗል።

ከዓመታት በፊት በደረሰበት አስከፊ የእሳት አደጋ ሙሉ አካሉ በእሳት ተቃጥሎ ህይወቱ ሊያልፍ ምንም አልቀራም ነበር።

የ6 ዓመቱ ህጻን ተሪ ማካርቲ በደረሰበት ከባድ የመቃጠል አደጋ ከ73 በመቶ በላይ ሰውነቱ ቆስሎ ለአንድ ሙሉ ዓመት በሆስፒታል አልጋ ላይ ተኝቶ አሳልፏል።

በህጻንነቱ የደረሰበት ያ አሰቃቂ አደጋ በአካሉ ላይ ዘላቂ ጠባሳዎችን ቢያስቀምጥም ተሪ ግን ህይወቱን በፍርሃት ውስጥ ሆኖ ለመምራት አልፈቀደም።

ለአካለ መጠን ሲደርስ ተሪ ህይወቱን ሙሉ በሙሉ የለወጠውንና የስነ ልቦና ፍርሃት ፈጥሮበት የነበረው "እሳት" ፊት ለፊት ለመጋፈጥ ወሰነ።

በጽኑ ውድድርና ስልጠና አልፎ በዋሽንግተን የስልጠና ማዕከል የበጎ ፈቃደኛ እሳት አጥፊ በመሆን ብቃቱን አስመስክሯል።

በስልጠና ወቅት ለመጀመሪያ ጊዜ እሳት ፊት ለፊት ሲቆም ፍርሃት ቢያናውጠውም "እሳት በእኔ ላይ ምንም አይነት የበላይነት የለውም" በማለት ፍርሃቱን ድል አድርጓል።

በአሁኑ ወቅት የራሱን ተሞክሮ በመጠቀም በእሳት አደጋ የተጎዱ ህጻናትን ለማገዝና የልጅነት ጊዜያቸውን በጥሩ ሁኔታ እንዲያሳልፉ በበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ተሰማርቶ ይገኛል።

በህይወታችን የሚያጋጥሙን ከባድ ፈተናዎችና ፍርሃቶች ለታላቅ አላማችን መነሻ ሊሆኑ ይችላሉ ሲል ተሪ ተናግሯል።

ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesge #fire #accident #emergency #hospital

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.