Logo
Getu Temesgen
በአሜሪካ የሺዎች ኢትዮጵያውያን የመኖር ተስፋ ተዘጋ
#ethiopia ​| በአሜሪካ የሚገኝ የፌደራል ፍርድ ቤት የትራምፕ አስተዳደር በሰብአዊ ምክንያት ለ5 ሺህ ገደማ ኢትዮጵያውያን ሰጥቶት የነበረውን ጊዜያዊ የጥበቃ ሁኔታ (TPS) እንዲያበቃ የሚፈቅድ ውሳኔ አሳለፈ።

የዲስትሪክት ፍርድ ቤት ዳኛ ብሪያን ኢ. መርፊ ለአፍሪካውያን ስደተኞች መብት የሚታገለው "አፍሪካን ኮሚዩኒቲስ ቱጌዘር" የተሰኘው ድርጅት የሕግ ክሱ ውሳኔ እስኪያገኝ ድረስ ጥበቃው እንዳይቋረጥ ያቀረበውን ጥያቄ ውድቅ አድርገውታል።

ውሳኔው በአሜሪካ ሕጋዊ የመኖርና የመሥራት መብት ተሰጥቷቸው የነበሩ በርካታ ሰዎችን ለስደት መባረር ስጋት የሚያጋልጥ ነው።

​በኢትዮጵያ በትግራይ ክልል ተከስቶ የነበረውን ግጭት ተከትሎ የባይደን አስተዳደር በ2022 ለኢትዮጵያውያኑ የ18 ወራት ጊዜያዊ ጥበቃ መስጠቱ ይታወሳል።

ይህ ጥበቃ በ2024 በወቅቱ የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትር አሌሃንድሮ ማዮርካስ ተራዝሞ የነበረ ቢሆንም የትራምፕ አስተዳደር የሀገር ውስጥ ደህንነት መስሪያ ቤት ጥበቃውን ለማቋረጥ እንቅስቃሴ ሲያደርግ ቆይቷል።

የኢትዮጵያውያኑ ጠበቆች የሀገር ውስጥ ደህንነት ሚኒስትሯ ክርስቲ ኖኤል ጥበቃውን የመሰረዝ ስልጣን የላቸውም እና ውሳኔው ሕገ-መንግስታዊ የመብት ጥሰት አለበት በሚል ያቀረቡትን አዲስ መከራከሪያ ዳኛ ውድቅ አድርገውታል።

​የመጠለያ ጥበቃው (TPS) ከጦርነት እና ሰብአዊ ቀውሶች ለሸሹ ሰዎች ያለመባረር ስጋት እንዲኖሩ የሚያስችል ቢሆንም የትራምፕ አስተዳደር ግን አሰራሩ ጊዜያዊ እንጂ ዘላቂ አለመሆኑን በመግለጽ የቀደሙ አስተዳደሮች ጥበቃውን በተደጋጋሚ ማራዘማቸውን ይነቅፋሉ።

በአሁኑ ወቅት የፌደራል ፍርድ ቤቶች ለሶማሊያ፣ ደቡብ ሱዳን እና ሀይቲ ስደተኞች ይሰጥ የነበረውን ተመሳሳይ ጥበቃ እንዲያበቃ መንገድ የከፈቱ ሲሆን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔም የሶሪያ እና የሀይቲ ስደተኞች ጥበቃ እንዲነሳ መፍቀዱ ይታወሳል።

📸 CNN

በያፌት ገ/ህይወት

Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.