ታሪክን ከዘመናዊነት ጋር፤ የኮሪደር ልማት ለኢትዮጵያ ቅርሶች
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 11፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) አንድ ሀገር የምትለካው በኢኮኖሚ ጥንካሬዋ ብቻ ሳይሆን ታሪኳን፣ ባሕሏንና ቅርሷን ጠብቃ ለወደፊቱ ትውልድ በሚመች መልኩ ለማስተላለፍ ባላት አቅም ጭምር ነው።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ በስፋት እየተተገበረ የሚገኘው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የከተሞችን መሠረተ ልማት ማሻሻል ብቻ ሳይሆን የሀገሪቱን ባሕላዊና ታሪካዊ ዕሴቶች ከአዲሱ የከተማ ውበት ጋር አስተሳስሮ የመያዝ ትልቅ ራዕይ ያለው ተግባር ነው።
ከዚህ ቀደም ትኩረት አጥተው የነበሩ ታሪካዊ ቅርሶችና ሕንፃዎች በኮሪደር ልማቱ አማካኝነት ግልጽና ተደራሽ እንዲሆኑ የተደረገ ሲሆን ይህም የከተሞችን ጥንታዊ አቀማመጥ ሳያጠፋ ከዘመናዊ የሥነ ሕንፃ ጥበብ ጋር አዋህዶ ለመጠበቅ የሚያስችል አዲስ መንገድ ከፍቷል።
በመንገድ ላይ የሚያልፍ ማንኛውም ዜጋም ሆነ እንግዳ የሀገሪቱን ባሕላዊ ሀብትና ታሪክ በቀላሉ እንዲገነዘብና የሀገሩን ማንነት በተሻለ መልኩ እንዲያውቅ ያደርጋል።
ወጣቱ ትውልድ ስለ ሀገሩ ታሪክና ባሕል በመጽሐፍት ብቻ ከመማር አልፎ በኮሪደር ልማቱ ከተካተቱ ታሪካዊ ቦታዎችና ከታደሱ መታሰቢያዎች በዓይኑ እያየና እየዳሰሰ እንዲያድግ እድል በመፍጠር ለሀገር ታሪክና ቅርስ ያለው ፍቅርና አክብሮት እንዲጎለብት ያደርጋል።
የኮሪደር ልማት ለውጭ ሀገር ቱሪስቶች ብቻ ሳይሆን ለሀገር ውስጥ ነዋሪዎችም አዳዲስ የጉብኝትና የመዝናኛ አማራጮችን በመፍጠር ዜጎች በሀገራቸው የሚገኙ ታሪካዊና ባሕላዊ ቦታዎችን በደስታና በምቾት እንዲጎበኙ መንገድ ከፍቷል።
ከዚህ በተጨማሪ የሀገር ውስጥ ቱሪዝም ባሕል እንዲያድግና ሕዝቦች የሌሎችን አካባቢዎች ታሪክና ባሕል በመጎብኘት እርስ በርሳቸው የሚቀራረቡበትን ማህበራዊ መሰረት ይፈጥራል።
በርካታ የተፈጥሮና የታሪክ ቅርሶች ያሏት ኢትዮጵያ የከተሞች መሠረተ ልማት አለመሟላት የቱሪስቶችን ቆይታ እንዲያጥር ያደርግ የነበረ ቢሆንም የኮሪደር ልማት የከተሞችን ጽዳት፣ ደህንነትና ውበት በማሻሻል ቱሪስቶች በከተሞች ውስጥ ረጅም ጊዜ እንዲቆዩና ዘና ብለው እንዲንቀሳቀሱ በር ከፍቷል።
በተጨማሪም በኮሪደሮች ላይ የተገነቡት ሰፊ የእግር መንገዶች፣ ፓርኮችና አደባባዮች ለተለያዩ ባሕላዊ ክስተቶችና የኪነጥበብ ዝግጅቶች ምቹ ስፍራዎችን በመፍጠር ልዩ ልዩ ሁነቶች በነፃነት የሚያቀርቡባቸው ክፍት መድረኮች እንዲበራከቱ አድርጓል።
በዚህም የኮሪደር ልማት ከቱሪዝም ዘርፍ የሚገኘውን የውጭ ምንዛሪና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነት በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግ የቻለ ነው።
ከዚህ በተጨማሪ ለቅርሶች የሚደረገውን እንክብካቤ ወቅታዊና ዘመናዊ በማድረግ ቅርሶች ከአደጋ፣ ከቆሻሻና ከተፈጥሮ ጉዳት የሚጠበቁበትን አሰራር አብሮ በመዘርጋት ታሪካዊ ሀብቶች ለክፍለ ዘመናት እንዲቆዩ በማድረግ ለወደፊቱ ትውልድ ትልቅ ሀገራዊ ውርስ ሆኖ እንዲሸጋገር ያረጋግጣል።
በቤተልሔም ግርማ

2 months ago