ሃገረ ህንድ የነጻነት በዓሏን በአዲስ አበባ አከበረች
#ethiopia | ነጻነት በነጻ የሚገኝ ሳይሆን በሚሊዮኖች መስዋዕትነት እና የህዝቦች ጽናት የሚረጋገጥ የህልውና መሠረት ነው።
በየዓመቱ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ነሃሴ 15 በሚከበረው የህንድ የነጻነት ቀን የሕንዳውያንን ነጻነት ቀን ብቻ ሳይሆን በ20ኛው ክፍለ ዘመን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለተቀሰቀሱ የፀረ-ቅኝ ግዛት ንቅናቄዎች ትልቅ የብርሃን ጭላንጭል ይዞ የመጣ ጭምር ነው።
የብሪታንያ ግዛት በህንድ ምድር መዋቅሩን የዘረጋው በ17ኛው ክፍለ ዘመን በ«ኢስት ኢንዲያ ካምፓኒ» በኩል በንግድ ስም ቢሆንም በሂደት ግን ንግዱ ወደ ፖለቲካዊና ወታደራዊ የበላይነት ተቀይሮ መላዋን ሀገር በብሪታንያ ዘውድ ስር እንዲወድቁ አደረገ።
በ1857 እ.ኤ.አ የተከሰተው የመጀመሪያው የሕንዳውያን ዓመፅ የቅኝ ግዛቱን ስርዓት ያናጋ ታላቅ ክስተት የነበረ ሲሆን ከዚያ በኋላ የነጻነት ትግሉ በተደራጀ መልኩ በፖለቲካ እና በማህበራዊ ንቅናቄዎች መመራት ጀመረ።
የህንድ የነጻነት ትግል በዓለም ታሪክ ልዩ የሚያደርገው የተለያዩ የትግል ስልቶች ተቀናጅተው የታዩበት በመሆኑ ነው።
ታላቁ መሪ ማሃትማ ጋንዲን ጨምሮ የህዝብ ንቅናቄ የመሩ የእርሳቸው የትግል ጓዶች አህጉር አቀፍ ንቅናቄዎች የብሪታንያን አስተዳደር ሙሉ በሙሉ ሽባ አድርገውታል።
በሌላ በኩል የነጻነት ንቅናቄው የፖለቲካ ፊት የነበሩት ጃዋሃርላል ኔህሩ ወጣቱን ትውልድ በማስተባበር እና በድርድር ጠረጴዛዎች ላይ የሕንዳውያንን ድምፅ በማሰማት ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል፤ እንዲሁም ሱብሃስ ቻንድራ ቦስ ደግሞ «የህንድ ብሔራዊ ሠራዊት» በመመስረት በወታደራዊ መንገድ የብሪታንያን የበላይነት ተጋፍጧል።
ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ማብቃት በኋላ የብሪታንያ ኢምፓየር ህንድን ይዞ ለማቆየት ያለው አቅም በመዳከሙ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ነሃሴ 15 ቀን 1947 እኩለ ሌሊት ላይ ህንድ ከ200 ዓመታት የብሪታንያ አገዛዝ በኋላ ነጻነቷን አወጀች።
በዚች ታሪካዊ ምሽት የህንድ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጃዋሃርላል ኔህሩ «ከዕድል ጋር የተደረገ ቀጠሮ» በሚለው ታዋቂ ንግግራቸው '' በዚህ እኩለ ሌሊት፣ ህንድ ወደ ህይወት እና ወደ ነጻነት ትነቃቃለች" ሲሉ አበሰሩ። ሆኖም የነጻነት ደስታው ከትልቅ ሀዘን ጋር የተቀላቀለ ነበር፤ ሀገሪቱ በሃይማኖታዊ መስመር ተከፍላ ህንድ እና ፓኪስታን በመባሏ በታሪክ ከተመዘገቡት ታላላቅ የህዝብ መፈናቀሎች እና የደም መፍሰሶች አንዱ ተከሰተ።
ዛሬ ላይ ይህ ታሪካዊ ቀን በህንድ በታላቅ ብሔራዊ ስሜት የሚከበር ሲሆን፣ በኒው ድልሂ በሚገኘው ታሪካዊው «ቀይ ምሽግ» ላይ የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር የህንድን ሶስት ቀለም ሰንደቅ ዓላማ የሚያሰቅሉበትና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች በቀለማት ያሸበረቁ ካይቶችን ወደ ሰማይ በመልቀቅ ነጻነታቸውን በደስታ የሚያከብሩበት ዕለት ነው።
ህንድ ነጻነቷን ስታገኝ ከፍተኛ ድህነት እና የኢኮኖሚ ውድቀት የነበረባት ብትሆንም ከሰባት አስርት ዓመታት በኋላ ግን ከአንድ ቢሊዮን በላይ ህዝቧን የምታስተዳድር የዓለማችን ትልቋ ዴሞክራሲያዊ ሀገር ከመሆኗም በላይ በህዋ ምርምር፣ በሶፍትዌር ኢንዱስትሪ እና በዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ ከታላላቅ ሀገራት ተሰላፊ ለመሆን በቅታለች።
በአጠቃላይ የህንድ የነጻነት ቀን የድል ታሪክ ብቻ ሳይሆን የብዙሃን ባህልና ቋንቋ ስብስብ የሆነች ሀገር «አንድነት በልዩነት ውስጥ» በሚል መርህ እንዴት ወደ ፊት መራመድ እንደምትችል ለዓለም ያሳየች ታላቅ ሀገር ናት።
በዛሬዎ ዕለትም ከነጻዋ ሀገር ከኢትዮጵያ ጋር የጸና ወዳጅነት የመሠረተችው ህንድ አዲስ አበባ በሚገኘው የህንድ ኤምባሲ የተለያዩ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የነጻነት በዓሏን አክብራለች።
ይህ ታሪካዊ ቀን ለሕንዳውያን የኋላ ታሪካቸውን የሚያስታውሱበት የዛሬውን እድገታቸውን የሚያከብሩበት እና የነገውን ብሩህ ተስፋቸውን የሚያልሙበት ታላቅ የብሔራዊ ኩራት ምልክት ነው።
📸 ከበደ መክብብ
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

2 months ago