ቱሪዝም፦ የተረሳው ጸጋችን ሲያብብ፤ የተሰበረው የድህነት ትርክት
*****************
(የዕለቱ መልዕክት)
ኢትዮጵያ ለዘመናት በ“ግብርና መር” እሳቤ ብቻ ተቆልፎ የነበረውን የኢኮኖሚ መዋቅር በመስበር፣ ቱሪዝምን እንደ አንዱና ዋነኛው የልማት ምሰሶ በማድረግ መጠቀም ጀምራለች፡፡
በታሪክ፣ በባህልና በተፈጥሮ ሃብት እጅግ የበለፀገችው ሀገራችን፣ ለረጅም ዘመናት ድንቅ ቅርሶቿ እንደ ሀብት ሳይሆን እንደ መከፋፈያ ዕዳ ሲታዩ ስሟም በረሃብና በችግር ትርክት ሲጠለሽ ቆይቷል።
ዛሬ ግን ይህ የድቅድቅ ጨለማ ትረካ በስትራቴጂካዊ መሪነትና በተጨባጭ ተግባር ተሰብሮ፣ ቱሪዝም የሀገር ግንባታ፣ የሰላም እና የኢኮኖሚያዊ ትንሣኤያችን አንቀሳቃሽ ሞተር ወደመሆን ተሸጋግሯል።
ባለፉት የለዉጥ ዓመታት የተመዘገቡት ስኬቶች ይህንን የፖሊሲ እመርታ በሚገባ ያረጋግጣሉ። “ገበታ ለሸገር”፣ “ገበታ ለሀገር” እና “ገበታ ለትውልድ” በሚሉ ሀገራዊ የሃብት ማሰባሰቢያ ፕሮጀክቶች እንደ እንጦጦ፣ ወንጪ፣ ጎርጎራ፣ ኮይሻ፣ቤኑና ፣ሎጎ ሀይቅ፣ ሃላላ ኬላ እና ሌሎችም ግዙፍ የኢኮ-ቱሪዝም መዳረሻዎች ተገንብተው ለአገልግሎት በቅተዋል።
በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በስፋት የተተገበሩት የኮሪደር ልማት ፕሮጀክቶችም፣ ከተሞቻችንን ለነዋሪዎችም ሆነ ለዓለም አቀፍ ቱሪስቶች እጅግ ምቹ፣ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና ማራኪ አድርገዋቸዋል። እነዚህ የህንፃና የፓርክ ግንባታዎች ብቻ ሳይሆኑ የሀገርን ኢኮኖሚ ወደ ተለያዩ የገቢ ምንጮች የማሸጋገር ግዙፍ የሥርዓት ለውጥ ማሳያዎች ናቸው።
በእነዚህ መጠነ-ሰፊ የመዳረሻ፣ የመሰረተ-ልማት እና የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስራዎች ምክንያት በቱሪዝም ዘርፉ ታይቶ የማይታወቅ አሃዛዊ ስኬት ተመዝግቧል። በዘንድሮው ዓመት ብቻ ከ1.4 ሚሊዮን በላይ የውጭ ጎብኚዎችን በመቀበል ከ5.2 ቢሊዮን ዶላር በላይ የውጭ ምንዛሬ ወደ ሀገር ማስገባት ተችሏል።
የሀገር ውስጥ ቱሪዝምም ከ50 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በማንቀሳቀስ ከ79 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ አስገኝቷል።
አዲስ አበባም የአፍሪካ የፖለቲካ መዲናነቷንና የተገነቡላትን ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ማዕከላት በመጠቀም፣ዘንድሮ ብቻ ከ204 በላይ ዓለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን በማስተናገድ የ"ማይስ" ቱሪዝም ማዕከል መሆኗን በተግባር አሳይታለች።
ለዚህ ስኬት የዲጂታላይዜሽን ሚና እጅግ ከፍተኛ ነው። የኢ-ቪዛ አገልግሎት መዘመኑ እንዲሁም እንደ ‘መሶብ’ ያሉ የተቀናጁ የዲጂታል መተግበሪያዎች ስራ ላይ መዋላቸው ቱሪስቶች ያለምንም እንግልት የትራንስፖርት፣ የሆቴል እና የመዳረሻ ትኬቶችን በዲጂታል መንገድ እንዲቆርጡ በማድረግ የጥሬ ገንዘብ አልባ ኢኮኖሚ ግንባታን እያፋጠነ ይገኛል።
በሌላ በኩል መንግስት ከ35 በላይ ተዘርፈዉ ወደ ውጭ የወጡ ታሪካዊ ቅርሶችን ወደ ሀገር ቤት በማስመለስ፣ የነበሩትን በማደስና አዳዲስ ቅርሶችን በዩኔስኮ በማስመዝገብ ያሳየው ጽኑ የዲፕሎማሲ ጥረት፣ ቅርሶቻችንን ውብ አድርጎ በማውጣት ሀብት እንዲያስገኙ አስችሏል።
ይህ ሁሉ ስኬት ዘላቂ የሚሆነው ግን እያንዳንዱ ዜጋ የአመለካከትና የአስተሳሰብ ለውጥ ሲያመጣ ብቻ ነው። ቱሪዝም የሁላችንም የጋራ ፕሮጀክት ነው። የታክሲ አሽከርካሪዎቻችን እንግዶችን ከኤርፖርት ሲቀበሉ የሀገራችንን መልካም ገጽታ የመግለጥ ጥበብ ሲላበሱ፣ የሆቴል ባለሙያዎቻችን ከፍተኛ የመስተንግዶ ደረጃን ሲጠብቁ እንዲሁም የጥበብ ሰዎቻችን የሀገራችንን ውብ ገፅታዎች በቀዳሚነት ሲያስተዋውቁ ዘርፉ ይበልጥ ያብባል።
እያንዳንዷን የተፈጥሮና የታሪክ ጸጋ ወደ ሃብት በመለወጥ የበለጸገች፣ የተለወጠችና የተከበረች ሀገር ለልጆቻችን ለማስረከብ ለሀገራችን አምባሳደር መሆን ይገባናል፡፡
ኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል

2 months ago