Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ከሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እያካሄደ በሚገኘው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ ላይ፣ በሃይማኖት ጉዳዮች እና በሰላም ግንባታ አጀንዳዎች ላይ ሲወያዩ የነበሩት ተመካካሪዎች ባቀረቧቸው ምክረ ሀሳቦች ላይ መግባባት ላይ መድረሳቸውን ዛሬ "በሰበር ዜና" አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ባወጣው ሰበር መረጃ መሰረት፣ ዛሬ ነሐሴ 5 ቀን 2018 ዓ.ም በእነዚህ ሁለት አጀንዳዎች ላይ ሲመካከሩ የቆዩት የሥራ ቡድኖች በተጠናቀሩት የጋራ ምክረ ሀሳቦች ላይ ሙሉ ስምምነት ላይ በመድረስ በተዘጋጀው ቃለ ጉባኤ ላይ ፊርማቸውን አኑረዋል። በኮሚሽኑ የአሰራር ሥነ-ዘዴ መሰረት የጉባኤው ተሳታፊዎች እያንዳንዳቸው 500 አባላት ባሏቸው ስምንት የተለያዩ የስራ ቡድኖች በመከፋፈል፣ በኮሚሽኑ ምክር ቤት በተለዩ ስምንት ዋና ዋና አጀንዳዎች ላይ ሰፊ ምክክር እያደረጉ ይገኛሉ።

በዚህም አሰራር እያንዳንዱ 500 አባላት ያሉት ቡድን በአንድ የተለየ አጀንዳ ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ እየተመካከረ ይገኛል። የሃይማኖት እና የሰላም ግንባታ አጀንዳዎችን ተከትሎ፣ በቀሪዎቹ ጉዳዮች ላይ እየተወያዩ የሚገኙት የሌሎች አጀንዳዎች ተመካካሪዎችም በቀጣዮቹ ቀናት በተመሳሳይ መልኩ የየአጀንዳ ሀሳቦቻቸውን የጋራ በማድረግ በቃለ ጉባኤዎቻቸው ላይ እንደሚፈራረሙ ይጠበቃል።

2 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.