በካናዳ የጥገኝነት ጥያቄ ካቀረቡ የአፍሪካ ሀገራት ሪፖርት ውረፈስጥ ኢትዮጵያም ተካታለች
#ethiopia | የካናዳ የኢሚግሬሽን እና የስደተኞች ቦርድ (IRB) እ.ኤ.አ በ2025 በካናዳ የጥገኝነት ጥያቄ ያቀረቡ አፍሪካውያንን በተመለከተ አዲስ መረጃ ይፋ አድርጓል።
ይፋ በሆነው መረጃ መሠረት በካናዳ ጥገኝነት በመጠየቅ ረገድ ናይጄሪያውያን በ21 ሺህ 573 ጥያቄዎች የአፍሪካን ቀዳሚ ስፍራ ሲይዙ፣ ጋና በ9 ሺህ 784 እንዲሁም ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በ6 ሺህ 752 የጥገኝነት ጥያቄዎች ሁለተኛ እና ሦስተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጠዋል።
የጥገኝነት ጥያቄዎች ዝርዝር ውስጥ አልጄሪያ በ5 ሺህ 821፣ ጊኒ በ4 ሺህ 709፣ ኬንያ በ3 ሺህ 862 እንዲሁም ካሜሩን እና ሴኔጋል እያንዳንዳቸው በ3 ሺህ 579 ጥያቄዎች በከፍተኛ ደረጃ ከተጠቀሱት ሀገራት መካከል ይገኙበታል።
በተጨማሪም ሩዋንዳ፣ ኮትዲቯር እና ኡጋንዳ በቅደም ተከተል ይከተላሉ።
ከምስራቅ አፍሪካ ሀገራት መካከል ኢትዮጵያ በ2 ሺህ 203 የጥገኝነት ጥያቄዎች በ12ኛ ደረጃ ላይ የምትገኝ ሲሆን፣ ቻድ፣ ቡሩንዲ፣ ግብፅ እና ቡርኪና ፋሶም በቅደም ተከተል የሚከተለውን ደረጃ ይዘዋል።
በአንጻሩ ሞሮኮ፣ ሱዳን፣ አንጎላ እና ቶጎ በቅደም ተከተል ከ900 እስከ 1,000 የሚደርሱ የጥገኝነት ጥያቄዎችን በማስመዝገብ በ20ሩ አፍሪካ ሀገራት ዝርዝር ማጠቃለያ ላይ ተቀምጠዋል።
በያፌት ገ/ህይወት
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu

3 months ago