Logo
YenetaTube
ኢራን "ሰላማዊ" የኒውክሌር መርሃ ግብር የማዘጋጀት "መብት" አላት ! ፑቲን ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን እና ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተቀሰቀሰበት እ.ኤ.አ. 2022 በኋላ የመጀመሪያ የስልክ ውይይት ማድረጋቸው ተነገረ ። በሁለቱ መሪወች ዉይይት በዩክሬን እና በሩሲያ መካከል ሶስት አመታትን ያስቆጠረዉ ጦርነት ወደ ዉይይት የሚያመራበትን የመፍትሔ ሀሳብና በኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ዙሪያ መወያየታቸው ነዉ የተገለጸው ። ፈረንሳይ ለዩክሬን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ያላትን የማይናወጥ ድጋፍ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩት የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በዩክሬንና ሩሲያ የተኩስ አቁም እና ግጭቱን ለማስቆም ድርድር እንዲጀመር ጥሪ ማቅረባቸውን የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ማክሰኞ አስታውቋል። የዩክሬን እና ሩሲያ ጦርነት የምዕራባውያን መንግስታት ፖሊሲ ቀጥተኛ ውጤት መሆኑን የተናገሩት ቭላዲሚር ፑቲን ምዕራባውያን መንግስታት "ለበርካታ አመታት የሩስያን የደህንነት ስጋትና የጸጥታ ፍላጎት ችላ ማለታቸዉ" እና "በዩክሬን ውስጥ ጸረ-ሩሲያ አስተሳሰብ እንዲሰርጽ ማድረጋቸው ወደጦርነቱ እንዲገቡ እንዳስገደዳቸው በመግለፅ የሰላም ስምምነቱን በተመለከተ "ሁሉን አቀፍ እና ረጅም ጊዜ የሚቆይ፣ የዩክሬን ቀውስ መንስኤዎችን ለማስወገድ የሚያስችል እና በአዳዲስ የክልል እውነታዎች ላይ የተመሠረተ" መሆን አለበት ብለዋል ። ማክሮን ለኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር፣ ሚሳኤሎች ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ለማምጣትና በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀረ-ሽብርተኝነት ስምምነት (NPT) የተጣለባትን ግዴታ እንድትወጣ እና ከአለም አቀፉ የአቶሚክ ኢነርጂ ኤጀንሲ (IAEA) ጋር ሙሉ በሙሉ እንድትተባበር ሩሲያ የማግባት ስራ እንድትሰራ ጥያቄ አቅርበዋል ። ፑቲን በበኩላቸው ኢራን "ሰላማዊ" የኒውክሌር መርሃ ግብር የማዘጋጀት "መብት" አላት ነገር ግን ህጋዊ በሆነ መልኩ ማካሄድ አለባት ብለዋል ። ስለ ውይይቱ በክረምሊን የተሰጠ መግለጫ እንዳስታወቀው ከሆነ ፕሬዚዳንቶቹ ኢራን ሰላማዊ የኒውክሌር ኃይልን የማልማት ህጋዊ መብትን ማክበር እና ከIAEA ጋር ትብብርን ጨምሮ በ NPT ስር የገባችውን ቃል መቀጠል አስፈላጊ መሆኑን መስማማታቸውን ገልጿል ። ሲል Xinhua የዜና አገልግሎት ዘግቧል። ዘገባው ሁለቱ መሪዎች ጥረታቸውን ለማስተባበር እና መፍትሄ ለማምጣት በቅርቡ በድጋሚ ለመነጋገር መስማማታቸው አክሎ ገልጿል ። የኔታ ትዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

12 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.