የኤሌክትሮኒክ ሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት ስለመጠቀም (በመመሪያ ቁጥር 1142/2018 መሠረት)‼️
1/ ከኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መመዝገቢያ ሥርዓት ጋር ተስማሚ የሆነ የኤሌክትሮኒክ ሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት መጠቀም በታክስ ሕጉ መሰረት የሂሳብ መዝገብ በሚይዙ ታክስ ከፋዮች ላይ ተፈጻሚ ነው።
2/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ የተደነገግው ቢኖርም ማንኛውም ታክስ ከፋይ በፈቃደኝነት ከኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ መመዝገቢያ ሥርዓት ጋር ተስማሚ የሆነ የኤሌክትሮኒክ ሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት መጠቀም ይችላል።
3/ በአባሪ ሁለት በተዘረዘሩት ዘርፎች የተሰማሩ ታክስ ከፋዮች የሚጠቀሙት የሽያጭ መመዝገቢያ ስርዓት ግዴታ ከቀጥታ ግንኙነት ውጭ የሚሰራ መሆን ይኖርበታል።
4/ በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 3 ላይ የተደነገግው ቢኖርም የታክስ ባለስልጣኑ ከቀጥታ ግንኙነት ውጭ የሚሰራ የሽያጭ መመዝገቢያ ስርዓት የመጠቀም ግዴታ የሚሆንባቸውን ዘርፎች ማሻሻል ይችላል።
5/ ግብር ከፋይ ፈቃድ የተሰጠውን የኤሌክትሮኒክ የሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት/ሶፍትዌር ወይም የኤሌክትሮኒክ የሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት አገልግሎት ወይም ታክስ ከፋዩ ለራሱ ብቻ የሚጠቀምበት የኤሌክትሮኒክስ የሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት ለመጠቀም፦
ሀ) በባለስልጣኑ የታክስ ከፋይ የድረ-ገጽ አገልግሎት ማዕከል ለኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ተጠቃሚነት በመመዝገብ የስርዓት መለያ ቁጥር ፣ የግንኙነት ቁልፍ እና የተጠቃሚ የሚስጥር ቁልፍ መውሰድ ይኖርበታል፣
ለ) በታክስ ከፋዩ ስም/የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር እና በተመዘገበው ሶፍትዌር/ስርዓት መለያ ቁጥር በመጠቀም የዲጂታል ፊርማ ሰርተፍኬት ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ወይም ፈቃድ ካለው አካል መውሰድ ይኖርበታል፣
ሐ) በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 2 “ሀ” እና “ለ” የተገኘውን መረጃ በመጠቀም የኤሌክትሮኒክ የሽያጭ መመዝገቢያ ሥርዓት/ሶፍትዌር ለስራ ዝግጁ በማድረግ መጠቀም ይችላሉ።
6/ ታክስ ከፋይ በተሰጠው የደረሰኝ ሶፍትዌር ፈቃድ በኢኮሜርስ ወይም ዲጂታል ገበያ ቦታ ለመጠቀም፦
ሀ) በባለስልጣኑ የታክስ ከፋይ የድረ-ገጽ አገልግሎት ማዕከል ለኤሌክትሮኒክ ደረሰኝ ተጠቃሚነት መመዝገብና የሚጠቀመውን ኢኮሜርስ ወይም ዲጂታል ገበያ ቦታ በማመላከት የተጠቃሚ የሚስጥር ቁልፍ ቃል መውሰድ ይኖርበታል፣
ለ) በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ ሀ የተገኘውን መረጃ በመጠቀም ኢኮሜርስ ወይም ዲጂታል ገበያ ቦታ ሥርዓት/ሶፍትዌር ለስራ ዝግጁ በማድረግ መጠቀም ይችላሉ።
Seledadotio

3 months ago