የአበጋር ሥርዓት ለሰላም …
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 29፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምን ለማስፈንና ብሔራዊ አንድነትን ለመገንባት በሚደረገው ወሳኝ የሀገራዊ ምክክር ሒደት ውስጥ፣ የሀገር በቀል ዕውቀቶችና የባሕላዊ ዕርቅ ሥርዓቶች ሚና በቀላሉ የሚታይ አይደለም።
ለዚህ ደግሞ በአማራ ክልል በወሎ አካባቢ ለዘመናት የዘለቀው እና ማሕበረሰባዊ መስተጋብርን በማጠናከር ረገድ ትልቅ አቅም ያለው የ“አበጋር” የባሕላዊ ዳኝነትና የሽምግልና ሥርዓት በምሳሌነት የሚጠቀስ ታላቅ የሀገር ሃብት ነው።
ይህ ሥርዓት ከግለሰቦች አለመግባባት ጀምሮ እስከ ደም መቃባት የደረሱ ከባድ ማሕበረሰባዊ ቀውሶችን ያለ ምንም የመንግሥት የኃይል መዋቅር፣ በእውነትና በፈሪሃ ፈጣሪ ላይ ብቻ ተመስርቶ የመፍታት ጥበብ ያለው ሥርዓት ነው።
አንዱ ወገን አሸናፊ ሌላኛው ደግሞ ተሸናፊ ሆኖ ስለሚወጣ ቁርሾውና ቂሙ ለትውልድ የመሸጋገር ዕድል ካለው የመደበኛው የፍርድ ቤት ክርክር የሚለየው የአበጋር ሥርዓት ዋነኛ ፍልስፍናው ‘ሁለቱም አሸናፊ’ የሚያደርገውን እና ሁለቱንም ወገኖች የሚያስማማ የፍትሕ መርህን ይከተላል።
በአበጋር ሥርዓት በዳይ ጥፋቱን አምኖ ይቅርታ የሚጠይቅበት፣ ለተበደለው አካልም ተገቢው ካሳ የሚሰጥበት እና ሁለቱም ወገኖች ቂማቸውን አጥፍተው ወደ ቀድሞው የማሕበራዊ ትስስር ሕይወታቸው የሚመለሱበት በመሆኑ የነገን ቁርሾ ከሥሩ ነቅሎ መጣል የሚያስችል ሥርዓት አለው።
ይህ ዓይነቱ ዘላቂ ሰላምን የማምጣት አቅም አሁን ሀገሪቱ ለምትገኝበትና ዘላቂ አንድነትን ለምትሻበት የሀገራዊ ምክክር ሒደት እጅግ ተፈላጊና መሠረታዊ ግብዓት የመሆን ከፍተኛ አቅም ይዟል።
ሌላው የአበጋር ሥርዓት መገለጫ ለፍትሕ መረጋገጥ የሚሰጠው ፍጹም ታማኝነትና ከማንኛውም ዓይነት ሙስና የጸዳ መሆኑ ሲሆን÷ በሥርዓቱ ውስጥ የሚሳተፉ ሽማግሌዎች የሰውን እጅ የማያዩ የእውነትና የሕሊና ሰዎች በመሆናቸው በማኅበረሰቡ ዘንድ ያላቸው ቅቡልነት እጅግ ከፍተኛ ነው።
ማኅበረሰቡ ለአበጋሮች ቃል የሚገዛበትና የሚታመንበት የሕግ ልቦና ያለው ይህ ሥርዓት የራሱ የሆነ ‘ቁና ሰፊ’ በመባል የሚታወቅ የሕግ አውጪ እና ‘ቁና ሰፋሪ’ በመባል የሚታወቅ ሕግ ተርጓሚ መዋቅር ያቅፋል።
ከዚህ በተጨማሪ በዓመት አንድ ጊዜ በመሰብሰብ ሕጉን የመከለስና ከዘመኑ ጋር በማስማማት ራሱን በራሱ እያደሰ የመጣ ሕያው የሕግ ተቋም መሆን ችሏል።
ይህ የባሕል ዕሴት ከማንነት፣ ከብሔርና ከሃይማኖት ልዩነት የጸዳ መሆኑ ለሀገራዊ ምክክሩ ያለውን ፋይዳ የጎላ ያደርገዋል።
ከየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል የመጣ ማንኛውም ሰው ችግር ሲገጥመው ያለ ምንም የባዕድነት ስጋት እኩል ፍትሕና አቀባበል እንዲያገኝ የሚያደርገው ሥርዓቱ ኢትዮጵያውያን የጋራ የሰላም እሴቶችና ታሪካዊ መስተጋብሮች እንዳሏቸው ትልቅ ማሳያ ነው።
በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ እያከናወነች በምትገኘው የሀገራዊ ምክክር ሒደት ውስጥ ስኬትን ለማስመዝገብ፣ እንደ አበጋር ያሉ የሀገር በቀል የግጭት አፈታትና የዕርቅ ሥርዓቶችን ማዕከል ማድረግ ይገባል።
እነዚህን እሴቶች በደንብ አጥንቶ፣ መዝግቦና አደራጅቶ መጠቀም የሕዝቦችን ዘላቂ ሰላምና አብሮነት ለማረጋገጥ ያለውን ሚና ከግምት ውስጥ በማስገባት እና ለእነዚህ የሀገር ሀብት ልዩ ትኩረትና ድጋፍ በመስጠት፣ ከማኅበረሰቡ ተሰሚነት ካላቸው የሀገር ሽማግሌዎች ጋር በቅንጅት መሥራት ያስፈልጋል።
የሀገር ሰላም እና አንድነት በዘላቂነት ሊረጋገጥ የሚችለው ከውጭ በሚመጡ ፍልስፍናዎች ሳይሆን፣ እንደ አበጋር ካሉ ከኢትዮጵያውያን ሥነ ልቦና፣ እምነትና ነባራዊ አስተሳሰብ ውስጥ ተጨምቀው ከወጡ የውስጥ የሰላም መሣሪያዎች ጋር ማስተሳሰር ሲቻል ነው።
በዮናስ ጌትነት

3 months ago