ኮሜርሻል ኖሚኒስ 60ኛ ዓመት በዓሉን በሩጫ አጠናቀቀ!
#fastmereja :-በሀገራችን የአውትሶርሲንግ (Outsourcing) ዘርፍ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ የሆነው ኮሜርሻል ኖሚኒስ፣ የምስረታ በዓሉ ማጠቃለያ የሆነውን ታላቅ የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ በዛሬዉ እለት በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት ተካሄደ።
«ለ60 ዓመታት የታማኝነት ጉዞ በጋራ እንሩጥ!» በሚል መሪ ቃል በተካሄደው በዚህ ስፖርታዊ መርሐ-ግብር ላይ የከተማ አስተዳደሩና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎችን ጨምሮ በርካታ ቁጥር ያላቸዉ ተሳታፊዎች ተገኝተዋል።
የኮሜርሻል ኖሚኒስ ዋና ስራ አስኪያጅ ኮማንደር ጥላቸው ፀጋዬ በዕለቱ እንደገለጹት፤ ሩጫው የ60 ዓመታትን የተቋማዊ ቅብብሎሽ ታሪክ ለማስታወስ ብቻ ሳይሆን፣ የተቋሙን ቀጣይ ግዙፍ የ10 እና የ20 ዓመታት የወደፊት ራዕይ ለህዝብ ለማስተዋወቅና የአዲስ አበባን ሰላምና ውበት ለአለም ለማሳየት ያለመ መልቲፕል (በርካታ) ዓላማዎች ያሉት መሆኑን ገልፀዋል።
ዋና ስራ አስኪያጁ አያይዘውም፣ ተቋሙ ከ60 ዓመታት ጉዞ በኋላ ወደፊት በ«ፒኤልሲ» ደረጃ ብቻ ሳይወሰን ወደ ግዙፍ የ«ኮሜርሻል ኖሚኒስ ግሩፕ» ለማደግ ስትራቴጂካዊ እቅዶችን ይዞ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ይፋ አድርገዋል።
ከተጠቀሱት አዳዲስና ግዙፍ ፕሮጀክቶች መካከል የአዋጭነት ጥናቱ የተጠናቀቀው የጋርመንት ፋብሪካ ግንባታ አንዱ ሲሆን፣ ይህም የድርጅቱን ዩኒፎርም ለባሽ ሰራተኞች ፍላጎት በራስ አቅም ለመሸፈንና ምርትን ወደ ውጭ በመላክ የውጭ ምንዛሬ ለማስገኘት የታለመ መሆኑ ነዉ የተገለፀዉ።
በተጨማሪም በደረቅ ቆሻሻ አስተዳደር ዘርፍ በመሰማራት «ከቆሻሻ ወደ ሀብት» ለመቀየር ጥናቶች እየተከናወኑ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅትም ለኮሪደር ልማቱ እገዛ የሚያደርግ በሰአት 60 ኪሎ ሜትር የሚሮጥ ዘመናዊ የፅዳት ማሽን ወደ ስራ መግባቱ የተገለፀ ሲሆን ድርጅቱ የራሱን ይዞታዎች በመጠቀም በሪል ስቴት ዘርፍ በስፋት ለመሳተፍ ዝግጅት እያደረገ እንደሚገኝም ተጠቁሟል።
በአሁኑ ወቅት ኮሜርሻል ኖሚኒስ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ 30 ቅርንጫፎቹ አማካኝነት ከ40 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ ሲሆን፣ ከነዚህም ውስጥ 42 በመቶ ያህሉ ሴቶች ናቸው።
ተቋሙ ወደፊት በሚያከናውናቸው አዳዲስ የኢንቨስትመንት ዘርፎች የሰራተኞቹን ቁጥር እስከ 120 ሺህ ለማድረስ እና በምስራቅ አፍሪካ ቀጣና ተወዳዳሪ ሆኖ ለመውጣት እየሰራ እንደሚገኝ ተገልጿል።

3 hours ago