(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካው ምክትል ፕሬዚዳንት ጄ.ዲ. ቨንስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን ጋር ያደረጉትን ስምምነት የሚቃወሙ የእስራኤል ጽንፈኛ ባለስልጣናትን አጥብቀው ተችተዋል። ቨንስ ለእስራኤል በሰጡት ማስጠንቀቂያ... ሀገሪቱ የሚያጋጥማትን እያንዳንዱን የደህንነት ችግር "በመግደል ብቻ" ልትፈታው እንደማትችል አሳስበዋል። ሐሙስ ዕለት ለኒውዮርክ ታይምስ በሰጡት ቃልም፣ "ትክክለኛው የመፍትሄ ሃሳባችሁ ምንድነው? ዘጠኝ ሚሊዮን ህዝብ ያላት ሀገር ናችሁ፤ እያንዳንዱን የብሄራዊ ደህንነት ችግር በመግደል ብቻ ልትፈቱት አትችሉም" በማለት ስምምነቱን የሚቃወሙትን አካላት ጠይቀዋል።
ምክትል ፕሬዚዳንቱ እስራኤል ለዲፕሎማሲ እድል እንድትሰጥ እና ለዋሽንግተን "ጥቂት እውቅና" እንድትሰጥ አሳስበዋል። በተጨማሪም ፕሬዚዳንት ትራምፕ አሁንም ከእስራኤል ጥቂት ታማኝ ደጋፊዎች አንዱ በመሆናቸው፣ የእስራኤል ባለስልጣናት በስምምነቱ ዙሪያ ትራምፕን በአደባባይ ከመተቸት እንዲቆጠቡ አስጠንቅቀዋል። ፕሬዚዳንት ትራምፕም ለእስራኤል አጠቃላይ ድጋፍ ቢኖራቸውም፣ በቅርቡ ከኔታንያሁ ጋር በስልክ በተነጋገሩበት ወቅት የእስራኤልን የሊባኖስ የጥቃት ስልት ተችተዋል። "አንድን ሰው በፈለጋችሁ ቁጥር አፓርታማ ማፍረስ አይጠበቅባችሁም፤ በእነዚያ አፓርታማዎች ውስጥ ብዙ ሰዎች አሉ፣ ሁሉም ደግሞ ሄዝቦላህ አይደሉም" በማለት ትራምፕ መናገራቸው ይታወሳል።
ይህ የአሜሪካ ባለስልጣናት አስተያየት የመጣው... በሁሉም ግንባሮች ጦርነት እንዲቆም የሚያሳስበው የአሜሪካ እና ኢራን የመግባቢያ ስምምነት ቢፈረምም፣ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ጦራቸውን ከሊባኖስ ለማውጣት ፈቃደኛ ባለመሆናቸውን ተከትሎ ነው። ኔታንያሁ የእስራኤል ጦር አስፈላጊ ሆኖ እስካገኘው ጊዜ ድረስ በደቡብ ሊባኖስ እንደሚቆይ አቋማቸውን አጽንተዋል። "በሰሜኑ ክፍል ደህንነትን እንመልሳለን" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለዚህም በደቡብ ሊባኖስ የደህንነት ቀጠና ማቆየት ግድ መሆኑን ተናግረዋል። ከንግግራቸው ጥቂት ቀደም ብሎም፣ የእስራኤል መከላከያ ሰራዊት (IDF) ወደ ሊባኖስ ግዛት 10 ኪሎ ሜትር ያህል ዘልቆ በመግባት የተቆጣጠረውን መሬት የሚያሳይ አዲስ ካርታ ያወጣ ሲሆን፣ የመከላከያ ሚኒስትሩ እስራኤል ካትዝም ጦሩ በሊባኖስ፣ ሶሪያ እና ጋዛ አስፈላጊ እስከሆነ ጊዜ ድረስ እንደሚቆይ ገልጸው ነበር።
ይህ የእስራኤል የጦርነት አቋም በሁሉም ግንባሮች ወታደራዊ ኦፕሬሽኖችን ማቆምን ከሚጠይቀው እና የሊባኖስን ሉዓላዊነት ከሚያከብረው የአሜሪካ እና ኢራን ስምምነት ጋር በቀጥታ ይጋጫል። የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባጋኢ በበኩላቸው፣ "የእስራኤል አገዛዝ በሊባኖስ ላይ የሚያደርሰው ጥቃት ከቀጠለ፣ ሌላኛው ወገን (አሜሪካ) በመግባቢያ ስምምነቱ የገባችውን ግዴታ እንደጣሰች ተደርጎ ይቆጠራል" በማለት ጠንከር ያለ ማስጠንቀቂያ ሰጥተዋል።

9 hours ago