"በምድር ላይ ከኖሩት ሁሉ እጅግ ኃያሉ ሰው እኔ ነኝ’" ትራምፕ
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ትላንት እኩለ ሌሊት ላይ በትሩዝ ሶሻል የማኅበራዊ ገጻቸው ባስተላለፉት ተከታታይ መልዕክቶች፣ "በዚህች ፕላኔት ላይ ከተራመዱት ሰዎች ሁሉ እጅግ ኃያሉ ሰው እኔ ነኝ" የሚል ይዘት ያለውን ጽሑፍ በማጋራት ከፍተኛ መነጋገሪያ ሆነዋል።
ትራምፕ ያጋሩት ጽሑፍ "የፕሬዝዳንታዊ ታሪክ ምሁር ዴቭ ኪንግ" በተባሉ ሰው የተጻፈ ሲሆን፣ ፕሬዝዳንቱን እንደ ታላቁ እስክንድር፣ ጄንጊስ ካን እና ናፖሊዮን ካሉ ታዋቂ የዓለም ታሪክ መሪዎች ጋር በማነጻጸር ከሁሉም እንደሚበልጡ ይገልጻል።
ይህ መግለጫ ይፋ የሆነው ትራምፕ ረቡዕ ዕለት ከአሜሪካ ጋር ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን የኢራን ጦርነት ለማቆም የሚያስችለውን ስምምነት በፈረሙ ማግስት ነው። ምንም እንኳን ይህ የሰላም ስምምነት በብዙ ወገኖች ዘንድ ከፍተኛ ትችት ቢሰነዘርበትም፣ ትራምፕ ግን እሳቸው ይህንን ስምምነት ባያደርጉ ኖሮ ዓለም "ከፍተኛ የኢኮኖሚ ቀውስ" ውስጥ ትወድቅ እንደነበር በመግለጽ ውሳኔያቸውን ተከላክለዋል።
ጽሑፉን ያዘጋጁት የታሪክ ምሁሩ ዴቭ ኪንግ፣ ትራምፕን እንደ አቲላ ዘ ሁን (Attila the Hun) እና ዊሊያም ዘ ኮንከረር ካሉ ታሪካዊ ኃያላን መሪዎች ጋር ጭምር በማወዳደር የእሳቸው ተፅዕኖ የላቀ እንደሆነ ይሞግታሉ። ይህ የትራምፕ የሌሊት ማኅበራዊ ሚዲያ ፖስት በአሜሪካ ፖለቲካና በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘንድ አሁንም ከፍተኛ ክርክርና መነጋገሪያነቱን ቀጥሏል።
Seledadotio

10 hours ago