(ዘ-ሐበሻ ዜና) የአሜሪካ የአረብ እና የአፍሪካ ጉዳዮች ከፍተኛ አማካሪ በዛሬው ዕለት በሰጡት ይፋዊ መግለጫ፣ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል እና በአጠቃላይ በአፍሪካ ቀንድ ለሚከሰቱ ግጭቶችና አለመረጋጋቶች ምክንያት በሆኑ የህወሓት ግለሰቦች ላይ የተጣለው ማዕቀብ፣ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለቀጠናው ሰላምና ደህንነት ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ መሆኑን አረጋግጠዋል።
አማካሪው አክለውም የአፍሪካ ህብረት የአፍሪካ ቀንድ ከፍተኛ ተወካይ የሆኑት ኦሉሴጉን ኦባሳንጆ፣ በህወሓት እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ለመፍታት እንዲሁም ሰላም እና መረጋጋትን ለማስፈን የሚያደርጉትን ጥረት አሜሪካ በደስታ እንደምትቀበለውና እንደምትደግፈው ገልጸዋል።
ይህ የአሜሪካ መግለጫ በክልሉ እያንዣበበ ያለውን አዲስ ውጥረት በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለመፍታት ግፊት እየተደረገ መሆኑን ያሳያል።
ስለዚህ የአሜሪካ አቋም እና ስለ አምባሳደር ኦባሳንጆ የሰላም ጥረት ምን ታስባላችሁ?

16 hours ago