Logo
SeledaPost
የኢትዮጵያ ስም የጣማቸው ትራምፕ አሁንም ስለግድቡ እየለፈፉ ናቸው!

በህዳሴ ግድቡ ዙሪያ አወዛጋቢ ንግግር የሚያደርጉት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ በድጋሚ "የግድቡን ጉዳይ አሁንም እናየዋለን፣ ለመፍታትም ጥረት እናደርጋለን" ሲሉ ተደምጠዋል።

በህዳሴ ግድብ ዙሪያ "ድርድር ለማስጀመር" ሁሉ ማቀዳቸውን እየተናገሩ ናቸው።

በፈረንሳይ የቡድን 7 ጉባዔ ላይ ከግብጹ ፕሬዝዳንት አብዱልፈታህ አል-ሲሲ ጋር የተገናኙት ትራምፕ፤ የዓባይ ግድብ "ውዝግብንም በድጋሚ ይጀመራል" ሲሉ ተደምጠዋል።

ከሁለትዮሽ ውይይት በኋላ “ከግብጹ ፕሬዝዳንት፣ ከጓደኛዬ ጋር በመሆኔ ታላቅ ደስታ ይሰማኛል። እሳቸው በመላው ዓለም የተከበሩ ናቸው... ግንኙነታችንም በግል ደረጃ ለረጅም ጊዜ በጣም ጠንካራ ሆኖ ቆይቷል" ሲሉ ተደምጠዋል።

ከአልሲሲ ጋር ጥሩ ወዳጅነት እንዳላቸው የገለፁት ትራምፕ፣ "ህዳሴ ግድብ በኢትዮጵያ ነው የተገነባው" በማለት ገልጸዋል።

"ግዙፍ ግድብ" ሲሉ በጠሩት የህዳሴ ግድብ ላይ "መፍትሔ የሚያመጣ ውይይት እናስጀምራለን" ያሉት ፕሬዝዳንቱ “የግድቡን ጉዳይ አሁንም እናየዋለን፣ ለመፍታትም ጥረት እናደርጋለን" ሲሉም ገልጸዋል።

"በኢትዮጵያ የተገነባው ግድብ በግብፅ ላይ ከፍተኛ ችግር እያስከተለ ነው" በማለትም የተለመደ ግጭት ቀስቃሽ ንግግር አድርገዋል።

ትራምፕ ለአል-ሲሲ ሲናገሩ "እውነቱን ማወቅ ከፈለጉ፣ በኢትዮጵያ ጉዳይ ላይ በጣም ኢ-ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ነው የተያዛችሁት ብዬ አስባለሁ" ሲሉ አነሳስተዋቸዋል።  #aljazeera

Seledadotio
Seledadotio
2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.