(ዘ-ሐበሻ ዜና) ጁን 15 ቀን 2026 እ.ኤ.አ. በጄኔቫ በተካሄደው የኤርትራ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ ውይይት ላይ፣ የኤርትራ አምባሳደር ሶፊያ ተስፋማርያም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዩ ሪፖርተር ያቀረቡትን ሪፖርት መሠረተ ቢስ እና ከእውነታው የራቀ ነው በማለት ውድቅ አድርገዋል።
አምባሳደሯ በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር የሪፖርቱ አዘገጃጀት (ሜቶዶሎጂ) ከፍተኛ ችግር ያለበት መሆኑን ተናግረዋል። ልዩ ሪፖርተሩ ያልተረጋገጡ እና ማንነታቸው ባልታወቁ ውጫዊ ምንጮች ላይ ብቻ ከመጠን ያለፈ ትኩረት ማድረጋቸውን የገለጹት አምባሳደሯ፣ በተቃራኒው በጤና፣ በትምህርት፣ በምግብ ዋስትና እና በመሠረተ ልማት ዘርፎች ኤርትራ ያስመዘገበችውን ዕድገት የሚያሳዩ የሌሎች የተመድ ተቋማትን እውነተኛ መረጃዎች ችላ ማለታቸውን ወቅሰዋል።
በኤርትራ ብሔራዊ አገልግሎት ዙሪያ በሪፖርቱ ለተነሳው ትችት ምላሽ የሰጡት አምባሳደር ሶፊያ፣ በአዋጅ ቁጥር 82/1995 መሠረት የተቋቋመው ይህ አገልግሎት የሀገርን ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነት እና ብሔራዊ ደህንነት ለማስጠበቅ የሚውል ተቋም መሆኑን አስረድተዋል። አገልግሎቱ ከተቀመጠው አስራ ስምንት ወራት በላይ ሊራዘም የቻለው በቀጣናው ባሉ ያልተፈቱ ውጥረቶች እና ተከታታይ የውጭ የጸጥታ ስጋቶች ምክንያት መሆኑንም ገልጸዋል። በርካታ የአውሮፓ ሀገራት ጭምር የውትድርና አገልግሎትን ዳግም እየመለሱ፣ እያሰፉ እና እየተወያዩበት ባለበት በአሁኑ ወቅት፣ ኤርትራ የራሷን የጸጥታ ሁኔታ መሠረት አድርጋ በምትወስነው የሉዓላዊነት መብት ላይ ብቻ ትችት መቅረቡ ተገቢ አለመሆኑን ተናግረዋል።
ከዚህም በተጨማሪ ልዩ ሪፖርተሩ ብቸኛው የክትትል ተቋም ነኝ ማለታቸው የዓለም አቀፉን የሰብዓዊ መብት ግምገማ ሥርዓት ያላገናዘበ መሆኑን እና ከእርሳቸው የተለየ አቋም የያዙ ሉዓላዊ የአፍሪካ ሀገራትን መተቸታቸው ከኃላፊነታቸው ውጪ መሆኑን አምባሳደሯ አውስተዋል። የአውሮፓ ኅብረትን ጨምሮ ሌሎች አካላት በቅንጅት ለሚያሳዩት የአቋም እና የድምጽ አሰጣጥ ተመሳሳይነት ትኩረት ሳይሰጥ፣ የአፍሪካ ሀገራት የተለየ አቋም ማንጸባረቃቸው እንደ ችግር መታየቱ አግባብነት እንደሌለውም ሞግተዋል።
ኤርትራ ባለፉት አስርት ዓመታት ከነበሩባት ጦርነቶች፣ ማዕቀቦች እና የውጭ ጫናዎች ባሻገር ሉዓላዊነቷን እና ማኅበራዊ መረጋጋቷን ጠብቃ ማቆየቷን፣ እንዲሁም መሠረታዊ አገልግሎቶችን መስጠቷን የቀጠለች መሆኗን የጠቀሱት አምባሳደር ሶፊያ፣ የሰብዓዊ መብት ምክር ቤቱ የቀረበውን የተዛባ ሪፖርት እና የውሳኔ ሃሳብ ውድቅ በማድረግ የልዩ ሪፖርተሩ የሥራ ጊዜ (ማንዴት) እንዲያበቃ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

3 days ago