Logo
YenetaTube
ከኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የተላለፈ የምክክር ተሳትፎ ጥሪ‼️

ሰኔ 8/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሀገሪቱ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በመላ ሀገሪቱ እንዲሁም በውጪ ከሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ያለመግባባት መንስኤ የሆኑ ጉዳዮችን በህዝባዊ ውይይት ሰብስቦ በሀገር አቀፍ ደረጃ ምክረሃሳብ የሚያሰናዳበትን ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ከሀምሌ 8/2018 ዓ.ም ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ ለማካሄድ ዝግጅቱን አጠናቋል።

በመሆኑም መላ ኢትዮጵያዊያን ለዚህ ታሪካዊ ሁነት መሳካት ከኮሚሽኑ ጎን በመሆን የሚጠበቅባችሁን እንድትወጡ ኮሚሽኑ ከወዲሁ ጥሪ ያቀርባል፡፡

በዚህ ታሪካዊ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ለመሳተፍ የተመረጣችሁ የማህበረሰብ ክፍሎችና የባለ ድርሻ አካላት ወኪሎችም ውጤታማ ሀገራዊ የምክክር ጉባኤ ማካሄድ የምትችሉበትን ሁለንተናዊ ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትጠብቁ ኮሚሽኑ ያሳስባል፡፡

የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን።

ሀገራዊ ምክክር ለሀገራዊ መግባባት‼️

3 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.