Logo
FastMereja
ዩኒቲ ብድርና ቁጠባ ዘመናዊውን የፋይናንስ ሥርዓት ቴክኖሎጂ በይፋ ሥራ ላይ አዋለ።

ዩኒቲ ብድርና ቁጠባ ተቋም በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ትግበራ ያስገባውን ዘመናዊ የባንክ ሥርዓት ቴክኖሎጂ ዛሬ ባካሄደው ደማቅ ሥነ ሥርዓት በይፋ መርቋል።

በዚህ የምረቃ መርሃ ግብር ላይ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ባለድርሻ አካላት፣ የተቋሙ የቦርድ አባላትና ሥራ አስኪያጆች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

ይህ አዲስ የቴክኖሎጂ ሥርዓት ሥራ ላይ መዋሉ ተቋሙ ለአባላቱ ፈጣን፣ ቀልጣፋ፣ አስተማማኝና ዘመናዊ የፋይናንስ አገልግሎት ለማቅረብ ለጀመረው የዲጂታል ሽግግር ጉዞ ትልቅ እርምጃ መሆኑ ተገልጿል።

ዩኒቲ ብድርና ቁጠባ በቀጣይም ተደራሽነቱን በማስፋትና አሠራሩን በማዘመን ለአባላቱ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት ያለውን ዝግጁነት አረጋግጧል።
#unitysavingandcredit #corebanking #digitaltransformation

4 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.