Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) የናይጄሪያዋ ሚኒስትር በአባ ሳሙኤል ወህኒ ቤት ተዘመረላቸው፡፡ የናይጄሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲኤታ ቢያንካ ኦጁኩዋ በዛሬው እለት በአዲስ አበባ ከተማ ወደሚገኘው አባ ሳሙኤል ወህኒ ቤት ጎራ ብለው ነበር፡፡ ልክ የወህኒ ቤቱን በር አልፈው እንደገቡ ግን ያልጠበቁት ገጥሟቸዋል፡፡ እስረኞቹ ሚኒስትሯን በማወደስ የዘመሩ ሲሆን በደስታም ጨፍረዋል፡፡

እነዚህ እስረኞች በስፍራው የሚገኙትና ቀሪ የእስር ዘመናቸውን በአገራቸው ውስጥ እንዲጨርሱ የተወሰነላቸው ናይጄሪያዊያን ናቸው፡፡ ሚኒስትር ዲኤታዋ በዚህ ሳምንት ወደአዲስ አበባ በማቅናት እስረኞቹ ወደአገራቸው በሚመለሱበት ሁኔታ ላይ ከኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ስምምነት መፈራረማቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡

ሚኒስትር ዲኤታዋ በአባ ሳሙኤል ያጋጠማቸውን በተመለተከ በኤክስ ገፃቸው ላይ ‹‹እጅግ ልብ የሚነካ ክስተት ነበር፡፡ ዜጎቻችን የሆኑት እስረኞቹ በጣም ተደስተዋል፡፡ ተስፋቸው ታድሷል›› ብለዋል፡፡ ወደአገራቸው የሚመለሱት 120 ያህል ፍርደኛ የሆኑ ናይጄሪያዊያን መሆናቸው ይታወቃል፡፡

6 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.