ጋና ከዩራጋይ የ2010 ዓለም ዋንጫ ሩብ ፍጻሜ ጨዋታ…
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 6፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) በፈረንጆቹ 2010 አፍሪካዊቷ ሀገር ደቡብ አፍሪካ የዓለም ዋንጫን ማዘጋጀቷ ይታወሳል፡፡
በ2010 ለመጀመሪያ ጊዜ በአፍሪካ አህጉር በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው ውድድር በሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር ጋና ከዩራጋይ ያደረጉት ጨዋታ በውድድሩ ከማይረሱ ክስተቶች መካከል አንዱ ነበር፡፡
በሶከር ሲቲ ስታዲየም አፍሪካዊቷን ሀገር ጋናን ከደቡብ አሜሪካዋ ሀገር ዩራጋይ ያገናኘው የሩብ ፍጻሜ ጨዋታ በመላው አፍሪካዊያን ዘንድ በጉጉት ነበር የተጠበቀው፡፡
አፍሪካ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ባዘጋጀችው የዓለም ዋንጫ ውደድር አዲስ የዓለም ዋንጫ ታሪክ በአፍሪካ ብሔራዊ ቡድን ሊጻፍ የተቃረበበት አጋጣሚ እንደነበርም ይታወሳል፡፡
በወቅቱ የጋና ብሔራዊ ቡድን የአፍሪካን በዓለም ዋንጫ ውድድር ከሩብ ፍጻሜ መሻገር ያለመቻል ታሪክ ሊቀይር መቃረቡም አይዘነጋም፡፡
ጨዋታው የሚደረግበት ሶከር ሲቲ ስታዲየም በቩቩዜላ ድምጽ የደመቀበት አጋጣሚ ይታወሳል፡፡
ጨዋታውን ጋና ማሸነፍ ብትችል አፍሪካ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ የዓለም ዋንጫን ማዘጋጀት ብቻ ሳይሆን በመድረኩ ግማሽ ፍጻሜ በመግባትም በዓለም ዋንጫ ውድድር አዲስ ምዕራፍ የምትከፍትበት ነበር፡፡
በጨዋታው ሁለቱም ብሔራዊ ቡድን ጥሩ እንቅስቃሴ ያሳዩ ሲሆን የመጀመሪያው አጋማሽ መጠናቀቂያ ላይ ሱሌ ሙንታሪ ግብ አስቆጥሮ ጋና 1 ለ 0 እየመራች ወደ መልበሻ ክፍል ማምራት ችለዋል፡፡
መላው አፍሪካውያን በሱሌ ሙንታሪ አማካኝነት ግቧ ስትቆጠር የነበራቸው ደስታ ወደር አልነበረውም፡፡
ከእረፍት መልስ 55ኛው ደቂቃ ላይ ዲያጎ ፎርላ ለዩራጋይ ብሔራዊ ቡድን ግብ በማስቆጠር ሀገሩን አቻ ማድረጉ ይታወሳል፡፡
የዩራጋይ ብሔራዊ ቡድን የፊት መስመር ተጫዋች ሉዊስ ሰዋሬዝ ኳስ በእጁ በመመለሱ ጋና የፍጹም ቅጣት ምት ብታገኝም አሳሞጂያን ሳይጠቀምበት መቅረቱ አይዘነጋም፡፡
አሳሞጂያን ሀገሩ ጋና ወደ ግማሽ ፍጻሜው የምታልፍበትን ዕድል መጠቀም ባለመቻሉ መላው አፍሪካዊያንን ያስቆጨ ክስተት ነበር፡፡
ጨዋታው 1 ለ 1 በሆነ አቻ ውጤት መጠናቀቁን ተከትሎ ወደ መለያ ምት ማምራታቸው ይታወሳል፡፡
በዚህም አሸናፊውን እና ግማሽ ፍጻሜውን የሚቀላቀለውን ብሔራዊ ቡድን ለመለየት በተሰጠው የመለያ ምት ዩራጋይ አሸናፊ ሆነች፡፡
አፍሪካም በዓለም ዋንጫ ታሪክ ግማሽ ፍጻሜ መድረስ ሳትችል በመቅረቷ መላው አፍሪካ ማዘኑ ይታወሳል፡፡
ከዚያ በኋላ ግን ሞሮኮ በ2022 የዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍጻሜ በመግባት በመድረኩ ግማሽ ፍጻሜ መድረስ የቻለች ቀዳሚዋ አፍሪካዊት ሀገር መሆን ችላለች፡፡
በወንድማገኝ ጸጋዬ

18 hours ago