ወደ ዋናው ምክክር - የሀገርን ምሶሶ በጋራ የመጠገን ታሪካዊ ጥሪ
***************
(የዕለቱ መልዕክት)
በሀገራችን የተጀመረው ሀገራዊ ምክክር ሂደት በታሪካችን፣ በማንነታችን እና በፖለቲካ አመለካከታችን ዙሪያ ለዘመናት የቆዩትን ስር የሰደዱ የፖለቲካ፣ የማህበራዊ እና የኢኮኖሚ ልዩነቶችን በሰለጠነ ውይይት ለመፍታት የሚደረግ ከፍተኛ እና ታሪካዊ ጥረት ነው።
ይህ ሂደት በተለይ በኢትዮጵያ አሁን ባለው ነባራዊ ሁኔታ ዘላቂ ሰላምን፣ መረጋጋትን እና ብሄራዊ መግባባትን ለማምጣት ትልቅ ሚና እየተጫወተ ይገኛል።
ለዓመታት ሀገርን እጅግ ከፍተኛ ዋጋ ሲያስከፍል የቆየውን እና ሀገራዊ አንድነታችንን ሲፈታተን የኖረውን "የእኔን ሃሳብ ካልተቀበላችሁ" የሚለውን የጥፋት የዜሮ ድምር አስተሳሰብ እና የጥርጣሬ ድባብ በመስበር፣ በጠመንጃ ሳይሆን በሀሳብ የበላይነት፣ በጠላትነት ሳይሆን በውይይት፣ እንዲሁም በሴራ ሳይሆን በግልጽነት ላይ የተመሰረተ የሰለጠነ የፖለቲካ ስርዓት ለመገንባት የተከፈተ ወሳኝ ምዕራፍ ነው።
ይህ ታሪካዊ አጋጣሚ የፈረሰውን ለመጠገን፣ የላላውን ለማጥበቅ፣ የቆዩ የፖለቲካ ቁስሎችን ለመፈወስና አዲስ የጋራ መጻኢ ዕድልን በጥንካሬ ለመንደፍ የቀረበ ወርቃማ እና ወደር የሌለው ሀገራዊ ዕድል ነው።
የሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሁሉንም የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሲቪክ ማህበራትን፣ የሃይማኖት አባቶችን፣ የሀገር ሽማግሌዎችን፣ እንዲሁም ልዩ ትኩረት በመስጠት የሴቶችና የወጣቶችን ድምፅ በማካተት ከመላው ሀገራችን በተሰበሰቡት አጀንዳዎች ላይ ከመጪዉ ሀምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዋናዉ ምክክር ለመጀመር ተዘጋጅቷል።
ይህ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት በአግባቡ ያሳተፈ ብሄራዊ መድረክ የምክክሩ እውነተኛ ባለቤትና መሪ ራሱ ህዝቡ እንዲሆን የሚያደርግ ከመሆኑም በላይ መሰረታዊ የልዩነት ነጥቦች ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኙና ዉይይት እንዲደረገባቸዉ ያስችላል።
በጥንቃቄ የተለዩት አጀንዳዎች የምክክሩን ዕድሜ፣ አቅጣጫ እና የመጨረሻ ውጤት የሚወስኑ ስለሆነ ዋነኛ ትኩረታቸዉ መሠረታዊ የልዩነት ነጥቦች ላይ ብቻ ማድረግ ምክክሩን ውጤታማ ያደርገዋል።
የምክክሩ መሳካት በዋና ዋና ብሄራዊ ጉዳዮች ላይ ዘላቂ መግባባት ላይ ለመድረስ፣ ህዝቡ በተለያዩ መንግስታዊ እና ህዝባዊ ተቋማት ላይ ያለው እምነት እንዲጠነክር፣ የፖሊሲ ማሻሻያዎች እንዲጠቆሙ እና ከዚህ ቀደም የነበሩ ቁስላችንን በራሳችን ውስጣዊ አቅምና መድኃኒት በመፈወስ የውጭ ጣልቃ ገብነትን በጽናት ለመግታት ያስችላል።
በጠረጴዛ ዙሪያ መቀራረብ እና መወያየት የሀገርን ሉዓላዊነት የማጽናት እና መረጋጋትን የማጠናከር የህልውና ጉዳይ ነው።
በዚህ ታላቅ የሀገር ግንባታ ሂደት ውስጥ የህብረተሰቡ አይንና ጆሮ የሆኑት የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የሃይማኖት እና የጦር ልሂቃን ያላቸውን ከፍተኛ ተሰሚነት፣ ተፅዕኖና እውቀት ተጠቅመው ህዝቡን በማንቃት ሂደቱን በቅንነት እና በዕውቀት የመምራትና የማገዝ ታሪካዊ ኃላፊነት አለባቸው።
በአሁኑ ወቅት ኮሚሽኑ በሩን ክፍት አድርጎ ሐሳብን ሲቀበል ቆይቶ ወደ መጨረሻው እና ወሳኙ ምዕራፍ ላይ የደረሰ በመሆኑ፣ ብሔራዊ ምክክሩ የፖለቲካ ምርጫ ሳይሆን የሀገር ህልውና ጉዳይ መሆኑን ሁላችንም ልንገነዘብ ይገባል።
የተበታተነ ሀሳብና ልዩነት ሀገርን ስለማያቆም እና ለጋራ መረጋጋት ስለማይበጅ፣ ሁላችንም እንደየድርሻችን ለብሔራዊ ጥቅማችን በጋራ ልንቆም እና ታሪክ ልንሰራ ይገባል።
በአንድነት መምከር፣ በልዩነት መከባበር፣ ለጋራ ውጤት በቅንነት መስራት እና ሀገራዊ ጥቅምን ማስቀደም የዘመኑ ታሪካዊ ጥሪ በመሆኑ፣ ኢትዮጵያ በልጆቿ እውነተኛ ምክክር፣ ይቅርታ እና መግባባት ትጸና ዘንድ ሁላችንም ለስኬታማነቱ በቁርጠኝነት ልንተጋ ይገባል።
የኢቢሲ ዶትስትሪም ኤዲቶሪያል
Ethiopian Broadcasting Corporation #ምክክር #ሐምሌ8 #ኢትዮጵያ #nationaldialogueethiopia

6 hours ago