የፋይዳ ተጨባጭ ስኬት የዲጂታል ኢትዮጵያ ውጤት ማሳያ ነው
********************
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (ፋይዳ) ባለፉት 5 ዓመታት የኢትዮጵያን የዲጂታል ምህዳር ቀይሯል። በፕሮግራሙ እስከአሁን ከ45.4 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የባዮሜትሪክስ መረጃቸው ተመዝግቦ የፋይዳ ቁጥር አግኝተዋል። አገልግሎቱ በከተሞች ሳይወሰን እስከ ቀበሌ መዋቅር በመውረድ ለአርሶ አደሩና ለአርብቶ አደሩ ተደራሽ ሆኗል።
ፋይዳ ከብሔራዊና ከግል ባንኮች ጋር በአደረገው ትስስር አዲስ አካውንት ለመክፈትና ማንነትን ለማረጋገጥ ዋነኛ ማረጋገጫ መንገድ ሆኖ እያገለገለም ነው። ይህም በሚሊዮን የሚቆጠሩ ዜጎች ወደ ፋይናንስ ሥርዓቱ እንዲገቡና የብድር ዕድል እንዲያገኙ ትልቅ እገዛ አድርጓል።
ከገቢዎች፣ ከትራንስፖርት፣ ከጤና ፣ ከውልና ማስረጃ እና ከተለያዩ ዘርፎች ጋር እንዲተሳሰር በመደረጉ አገልግሎቶችን በዲጂታል መንገድ እያሳለጠ ይገኛል። ቴክኖሎጂው የሐሰተኛ ሰነድ ዝግጅትንና ማጭበርበርን በመከላከል ረገድ ጉልህ ድርሻ አለው።
አዲሱ የዲጂታል 2030 ዕቅድም 100 በመቶ የጂዲታል ቴክኖሎጂ ተደራሽነትን በማለም የስኬት ፍሬዎችን ለሁሉም ዜጋ ለማድረስ በትኩረት እየተሠራበት ይገኛል።
ፋይዳ ባለፉት ዓመታት ከመታወቂያነት ባለፈ ለኢትዮጵያ ዘመናዊ የኢኮኖሚ ሥርዓት ግንባታ እንደ ዋነኛ መሠረት ተደርጎ እየተሰራበት ይገኛል። ይህ የዲጂታል ለውጥ ጉዞም ቀልጣፋ አገልግሎት በመስጠት የዜጎችን ሕይወት በእጅጉ እያሻሻለ ነው።
በመሀመድ ፊጣሞ
{#id:2647#} {#id:5682#} {#id:6339#} #id

15 hours ago