ብሔራዊ የሰላም በጎ ፈቃድ አገልግሎት ኅብረ-ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ ነው - የሰላም ሚኒስቴር
************************
ብሔራዊ የሰላም በጎ ፈቃድ አገልግሎት ኅብረ-ብሔራዊ አንድነትን በማጠናከር ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን የሰላም ሚኒስቴር የሰላም ግንባታ እና ብሔራዊ መግባባት ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) ገለፁ፡፡
የሰላም ሚኒስቴር ከክልል እና ከተማ አስተዳደር የሰላም እና ፀጥታ መዋቅር አካላት፣ ወጣቶች እንዲሁም ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ሚኒስቴሩ እያከናወናቸው ባሉ ብሔራዊ የሰላም በጎ ፈቃድ አገልግሎት እና በቀጣይ አገልግሎቱ በቅንጅት ተጠናክሮ በሚቀጥልበት መንገድ ዙሪያ ውይይት ተካሄዷል፡፡
በውይይቱ ላይ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) እንደገለፁት፤ ባለፉት ዓመታት "በጎነት ለአብሮነት" በሚል መሪ ሐሳብ ከመቶ ሺህ በላይ ወጣቶችን በሰላም ብሔራዊ በጎ ፈቃድ አገልግሎት በማሠልጠን እና ከተወለዱበት እና ካደጉበት አካባቢ ውጪ ለማሰማራት በተከናወነው ተግባር ወጣቶች ብዝሃ-ባህል፣ ብዝሃ-ቋንቋ እና ህብረ-ብሔራዊ ግንዛቤ እና ክህሎታቸውን ማሳደግ ተችሏል።
በዚህም በሕዝቦች መካከል ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ማጠናከር እንደተቻለ ተናግረዋል።
ዩኒቨርስቲዎች፣ መላው ህዝብ እና የክልል እና ከተማ አስተዳደሮች የሰላም እና ፀጥታ መዋቅሮች ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል ያሉት ሚኒስትር ዴዔታው አብሮነትንና ጠንካራ ሀገረ መንግስት የመገንባት ሂደቱን ለማጠናከር ብሔራዊ የሰላም በጎ ፈቃድ አገልግሎቱን ከክልል እና ከተማ አስተዳደሮች ጋር በቅንጅት የመስራት ሂደቱን ሚኒስቴሩ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።
በመድረኩ የተገኙ የክልል እና ከተማ አስተዳደሮች የሰላምና ፀጥታ መዋቅሮች፣ ወጣቶች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት አገልግሎቱ ማህበራዊ ትስስርን፣ ሰላም እና የህዝቦችን አብሮነት ለማጠናከር ጉልህ ሚና እየተጫወተ በመሆኑ ከሚኒስቴሩ ጋር በቅንጅት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
የሰላም ሚኒስቴር በቀጣይ ክረምት ወጣቱን በማንቀሳቀስ ብሔራዊ የሰላም በጎ ፈቃድ አገልግሎትን በሀገር አቀፍ ደረጃ በልዩ ንቅናቄ ለማከናወን በቅንጅት አንደሚሰራ ከሰላም ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
#ethiopianbroadcastingcorporation #unity #ethiopia #volunteerism

14 hours ago