Logo
SeledaPost
ዶናልድ ትራምፕ ከኢራን  ጋር የተፈጠረው ግጭት ማክተሙንና ታሪካዊ ስምምነት ላይ መደረሱን አስታወቁ

ትራምፕ ለሴኔት እጩ ባሪ ሙር በተዘጋጀ የድጋፍ መድረክ ላይ እንደተናገሩት፣ ስምምነቱ ዋሽንግተን የጠየቀቻቸውን ነጥቦች በሙሉ ያካተተ ነው።

​በዚህም መሰረት ቴህራን የኑክሌር መሣሪያን በጭራሽ ላለማልማትና ላለመግዛት ተስማምታለች።

ስምምነቱ ሲፈረምም ስትራቴጂካዊው የሆርሙዝ ሰርጥ  በይፋ ክፍት እንደሚሆንና የአሜሪካ ወታደሮች ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ተገልጿል።

ስምምነቱ በሳምንቱ መጨረሻ በአውሮፓ ምድር በምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ፊት ሊፈረም እንደሚችል ይጠበቃል።

​ሆኖም ዋሽንግተን ይህንን እንደ ታላቅ የዲፕሎማሲ ድል ብታቀርበውም፣ ከኢራን በኩል እስካሁን ይፋዊ ማረጋገጫ አልተሰጠም።

  ስምምነቱ የእስራኤሉን ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁንም ጭምር ያስገረመ መሆኑ ተገልጿል።

Seledadotio
Seledadotio
7 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.