Logo
SeledaPost
ዶናልድ ትራምፕ «የዋጋ ንረቱን እወደዋለሁ» ማለታቸው  ውዝግብ ፈጥሯል
 
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ባለፈው ወር የአሜሪካ የሸቀጦች ዋጋ ባለፉት ሶስት ዓመታት ውስጥ በከፍተኛ ፍጥነት መጨመሩን የሚያሳዩ ይፋዊ መረጃዎች ከወጡ በኋላ ›› የዋጋ ንረቱን እወደዋለሁ››ሲሉ ተደምጠዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የሰራተኞች ስታቲስቲክስ ቢሮ (BLS) የግንቦት ወር መረጃ እንደሚያሳየው ባለፉት 12 ወራት ውስጥ የዋጋ ንረቱ በ4.2 በመቶ  ጨምሯል ይህም  በሚያዝያ ወር ከነበረበት 3.8 በመቶ  ከፍ ያለው ይህ የዋጋ ጭማሪ  በዩኤስ-እስራኤል እና በኢራን መካከል ከተቀሰቀሰው ጦርነት ማግስት በናረው  የነዳጅ  አቅርቦት ዋጋ ሳቢያ የመጣ ነው።

ትራምፕ በነጭ ቤተ መንግስት በሰጡት መግለጫ «እወደዋለሁ  ቁጥሮቹ በጣም ጥሩ ነበሩ  ምን እንደምወድ ታውቃላችሁ? የዋጋ ንረቱን እወደዋለሁ» ሺሉ ተደምጧል ።

ነገር ግን ከኢራን ጋር ያለው ጦርነት ሲያበቃ የናረው ዋጋ «እንደ ድንጋይ ቁልቁል እንደሚምዘገዘግ   ወይም በከፍተኛ ሁኔታ እንደሚቀንስ» ቃል ገብተዋል።
 
ነገር ግን ትራምፕ ቆየት ብለው ለኒው ዮርክ ፖስት (New York Post) በሰጡት አስተያየት ንግግራቸው ከዐውደ-ጽሑፉ ውጪ እንደተወሰደባቸው ገልጸው  ማለት  የፈለጉት የዋጋ ንረቱ ከዚያ በላይ ባለመጨመሩ የተሰማቸውን ደስታ እንደሆነ አስረድተዋል።

ትራምፕ ለጋዜጣው  ሲናገሩ «የዋጋ ንረቱን ቁጥሮች የወደድኩት እኔ ከማወራው ነገር አንጻር ምክንያቱም  በጦርነት ውስጥ ብንሆንም እንኳ ቁጥሮቹ አስቀድሞ ከተገመተው በላይ እጅግ ዝቅተኛ መሆናቸውን ነው ስለዚህ  ከጦርነቱ ስንወጣ  ቁጥሮቹ ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ከነበሩበት ደረጃም በታች ዝቅ ይላሉ» ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ በቅርብ የወጡትን የዋጋ ንረት መረጃዎች አስመልክተው በቅድሚያ በሰጡት አስተያየት  የአሜሪካ ጦር ኃይሎች ከኢራን  በሚሊዮኖች የሚቆጠር  በርሜል  ዘይት ለመውሰድ የሌሊት ዘመቻዎችን ማካሄዳቸውን የገለጹ ሲሆን፣ ይህም ለነዳጅ ዋጋ መጠነኛ መቀነስ አስተዋጽኦ ማድረጉን ተናግረዋል።

አክለውም«ይህ ግጭት ሲያበቃ… የነዳጅ ዋጋው  ቀደም ሲል ወደነበረበት ደረጃ  ሲወርድ ታያላችሁ» ብለዋል።

ፕሬዝዳንቱ እ.ኤ.አ. በ2026 መጀመሪያ ላይ ወደ አዮዋ (Iowa) ያደረጉትን ጉዞን  በማስታወስ አንድ ጋሎን ቤንዚን በ1.85 ዶላር ሲሸጥ ማየታቸውን ጠቅሰው «በጣም በቅርቡ ወደዚያ ደረጃ እንመለሳለን» ሲሉ አክለዋል።

ይሁን እንጂ የዓለም አቀፉ የነዳጅ ዋጋ መመዘኛ የሆነው ብሬንት ክሩድ (Brent crude) አሁንም ቢሆን ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት ከነበረበት ደረጃ በከፍተኛ ሁኔታ ከፍ ብሎ እየተገበያየ ይገኛል።

 Seledadotio
Seledadotio
8 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.