Logo
Zehabesha
(ዘ-ሐበሻ ዜና) በቃሊቲና አባ ሳሙኤል ወህኒ ቤት የሚገኙ ናይጄሪያዊያንን ወደአገራቸው ለመመለስ የሚያስችል ስምምነት ተፈፀመ፡፡ የኢትዮጵያ መንግስትና የናይጄሪያ መንግስት በዛሬው እለት በቃሊቲና አባ ሳሙኤል ወህኒ ቤቶች የሚገኙ ናይጄሪያዊያን አስረኞችን በተመለከተ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ በስምምነቱ መሰረት 100 የሚሆኑትን የተፈረደባቸው ናይጄሪያዊያን ቀሪ የእስር ጊዜያቸውን በናይጄሪያ ወህኒ ቤት የሚያሳልፉ ይሆናል፡፡

ለዚሁ ጉዳይ ሲሉ ወደአዲስ አበባ የተጓዙት የናይጄሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯ ብላንካ ኦዱሚጉ ኢጁክዉ በኤክስ ገፃቸው ላይ ‹‹ፕሬዝደንት ቦላ አህመድ ቲኒቡን በመወከል ለዚህ ትልቅ ምእራፍ ለኢትዮጵያ መንግስትና ህዝብ ልባዊ አድናቆታችንንና ምስጋናችንን ለመግለፅ እወዳለሁ›› ብለዋል፡፡ ይህ ድርድር ከተጀመረ መቆየቱን ጠቅሰውም የመጨረሻ ስምነነት ላይ እስኪደረስ ባለው ጊዜ 4 ናይጄሪያዊያን እስረኞች ህይወታቸው ማለፉን አስረድተዋል፡፡

ስምምነቱንም ‹‹በሁለቱ አገራት መካከል ባለው የሰብአዊነት፣ የፍትህና የትብብር መርሆዎች ላይ የተመሰረተ ነው›› ብለውታል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ናይጄሪያዊያን ለእስር የሚዳረጉት በአብዛኛው አደንዛዥ እፅን በአዲስ አበባ በኩል አድርገው ወደመካከለኛው ምስራቅና አውሮፓ ለማሳለፍ በሚሞክሩበት ወቅት ነው፡፡ በአሁን ወቅት ከ300 በላይ ናይጄሪያዊያን በኢትዮጵያ ውስጥ በእስር ላይ የሚገኙ ሲሆን ሚኒስትሯ እንደገለፁት ዛሬ ስምምነት ላይ የደረሱት 100 የሚሆኑት ፍርደኛ በሆኑ ዜጎቻቸው ነው፡፡

2 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.