አዲስ የኢትዮጵያ መገለጫ እየሆነ የመጣው የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር
አዲስ አበባ፣ ሰኔ 3፣ 2018 (ኤፍ ኤም ሲ) የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በዓለም መድረክ አዲስ የኢትዮጵያ መገለጫ እየሆነ መጥቷል አለ የግብርና ሚኒስቴር።
በሚኒስቴሩ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃና አጠቃቀም መሪ ስራ አስፈፃሚ ፋኖሴ መኮንን ከፋና ፖድካስት ጋር ባደረጉት ቆይታ÷ ቀደም ሲል የሀገሪቱ የደን ሽፋን ከነበረበት 40 በመቶ ወደ 2 ነጥብ 7 በመቶ አሽቆልቁሎ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡
አሁን ላይ ግን የደን ሽፋኑ የአረንጓዴ ዐሻራ ብሔራዊ ንቅናቄ ሲጀመር ከነበረበት 17 ነጥብ 2 በመቶ ወደ 23 ነጥብ 6 በመቶ ማደግ መቻሉን ገልጸዋል።
ስኬቱ በእውቀት ላይ በተመሰረተ ሕዝባዊ ተሳትፎ በመመራቱ ችግኝ መትከልን ከመርሐ ግብርነት ወደ ዘላቂ የማህበረሰብ ባህል በመቀየር የባለቤትነት ስሜትን አጠናክሮታል ብለዋል።
መርሐ ግብሩ ድርቅን በመከላከል፣ የአፈር መሸርሸርን በመቀነስና ምርታማነትን በመጨመር ረገድ በብዝሃ ዘርፍ ከፍተኛ የኢኮኖሚ ለውጥ ያመጣ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
ለትውልድ ታስቦ በእቅድ እየተመራ ባለው በዚህ መርሐ ግብር ለ8ኛው ምዕራፍ፣ 8 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞችን ለመትከል 8 ነጥብ 6 ቢሊየን ችግኞች መዘጋጀቱን ጠቅሰዋል፡፡
ለችግኝ ተከላ የቦታ መረጣና የጉድጓድ ዝግጅትም አስቀድሞ መጠናቀቁን አስታውቀዋል።
ከችግኝ ዝግጅቱ 40 በመቶ ሀገር በቀል መሆኑን ገልጸው÷ ቀሪው 60 በመቶ ደግሞ ዘርፈ-ብዙ ጠቀሜታ ያላቸው የፍራፍሬ፣ የመኖ፣ የደን እና የውበት በመሆናቸው ማህበረሰቡን በቀጥታ ተጠቃሚ ያደርጋሉ ብለዋል።
በዘንድሮው የአንድ ጀንበር ታሪካዊ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርም 800 ሚሊየን ችግኞች እንደሚተከሉ ገልጸዋል።
በቅድስት ዘወዱ
አቶ ፋኖሴ መኮንን ከፋና ፖድካስት ጋር ያደረጉትን ቆይታ ማስፈንጠሪያውን በመጫን ይመልከቱ👇
https://www.youtube.com/wa...

9 days ago