Logo
FastMereja
በጋምቤላ ከተማ ተከስቶ የነበረው የተኩስ ልውውጥ

​#fastmereja I ዛሬ ማምሻውን በጋምቤላ ከተማ በአንድ የፌዴራል ፖሊስ አባል አማካኝነት ተከስቶ የነበረው ያልተጠበቀ የተኩስ ክስተት በቁጥጥር ሥር መዋሉንና በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው ሙሉ መረጋጋት መስፈኑን የክልሉ መንግሥት በሰጠው ወቅታዊ መግለጫ አስታውቋል።

​የክልሉ መንግሥት ዛሬ ሰኔ 1 ቀን 2018 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ ክስተቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ የክልሉና የፌዴራል ፀጥታ አካላት በቅንጅት ባደረጉት ፈጣን እንቅስቃሴ ሁኔታው ወደ ከፋ ደረጃ እንዳይሸጋገር ማድረግ ተችሏል። በማረጋጋት ሂደቱ ወቅት የተኩስ ልውውጥ እንደነበረ የተገለጸ ሲሆን፣ በአሁኑ ሰዓት ግን ውጥረቱ ሙሉ በሙሉ ረግቦ አካባቢው ወደ መደበኛ እንቅስቃሴው ተመልሷል።

​የክልሉ መንግሥት ከጉዳዩ ጋር ተያይዘው ያሉ ዝርዝር ምክንያቶች በሕግና በሥርዓት ተጣርተው ተገቢው እርምጃ እንደሚወሰድ ያረጋገጠ ሲሆን፣ የፀጥታ አካላትም አስፈላጊውን የጥበቃና የክትትል ሥራ በቀጣይነት እንደሚያከናውኑ አስታውቋል።

6 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.