Logo
YenetaTube
የኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል በሮምና ሞስኮ...

ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሳምንቱ በሮም እና በሞስኮ በተካሄዱ ውድድሮች ላይ በበላይነት አጠናቅቀዋል።

በሩሲያ ሞስኮ በተካሄደውና በዓለም አትሌቲክስ የኤፍ ደረጃ በተሰጠው የ2026 የዝናሜንስኪ ወንድማማቾች መታሰቢያ የአትሌቲክስ ውድድር የኢትዮጵያ አትሌቶች የበላይነት በመያዝ ውድድሩን በታላቅ ድል ማጠናቀቅ ችለዋል።

በሴቶች የ1 ሺህ 500 ሜትር ውድድር አትሌት ብርቄ ኃይሎም 1ኛ በመሆን ማጠናቀቅ ስትችል÷ አትሌት ሳሮን በርሃ ደግሞ 2ኛ ደረጃን ይዛለች።

አትሌት ደስታ ታደለ 5ኛ፣ አትሌት ሲፈን ዳገታ 8ኛ ፣ አትሌት በሻቱ ጌታ 9ኛ እና አትሌት ቤተልሔም ሙላት 15ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል።

የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ውድድር አትሌት ፈንታዬ ጫኔ በአንደኝነት ስታሸንፍ÷ አትሌት ቤተልሔም ኦላና 2ኛ ወጥታለች።

አትሌት ሰላማዊት ሻምበል 4ኛ እንዲሁም አትሌት ትርንጎ ታዳለ 6ኛ ደረጃን ይዘው አጠናቅቀዋል።

በ3 ሺህ ሜትር መሰናክል አትሌት ብርቱካን ገዳሙ ፈጣን ፉክክር በተደረገበት የሩጫ መድረክ ርቀቱን 2ኛ ደረጃን ይዛ አጠናቅቃለች።

በ800 ሜትር አትሌት ሀብታም ገበየሁ 6ኛ ደረጃን መያዝ ችላለች።

በወንዶች የ10 ሺህ ሜትር ውድድር ላይ አትሌት እዮብ ስመኝ በበላይነት ጨርሷል፡፡

በዚሁ ውድድር ሌላኛው ኢትዮጵያዊ አትሌት ሽመልስ ንጉሴ 3ኛ ደረጃን በመያዝ ፈፅሟል።

የወንዶች 3 ሺህ ሜትር መሰናክል አትሌት ዲንቃ ፍቃዱ 1ኛ በመሆን ሲያሸንፍ÷ አትሌት ሂርኮ ኃይሉ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቅቋል።

የ2026 ዳይመንድ ሊግ 4ኛ መዳረሻ በሆነው የሮሙ የሴቶች 5 ሺህ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የመጀመሪያዎቹን ሰባት ደረጃዎች በመቆጣጠር ጨርሰዋል፡፡

አትሌት ልቅና አምባው 14፡18፡41 የሆነ የወቅቱን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ባለድል ሆናለች።

FBC

13 hours ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.