Logo
Getu Temesgen
ለኮሪደር ልማት አገልግሎት በመስጠት ላይ የነበረ የኤሌክትሪክ ገመድ የሰረቀ ግለሰብ በፖሊስ አባላት እጅ ከፍንጅ ተያዘ
#ethiopia | በረከት አረጋ የተባለ ግለሰብ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመው በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው ጉስቋም ቅድስት ማርያም አካባቢ ከምሽቱ 4:00 ሠዓት ላይ ነው።

ተጠርጣሪው በሠዓቱ ለኮሪደር ልማት ተዘርግቶ አገልግሎት እየሰጠ የሚገኝ የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ኬብል በመጋዝ ቆርጦ በመውሰድ በውሃ ፍሳሽ መውረጃ ቱቦ ውስጥ ገብቶ ለመሰወር ቢሞክርም በወቅቱ ስራ የነበሩ የፖሊስ አባላት ተከትለው በመግባት ሁለት ሰአት በፈጀ ፍለጋ ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጦር ስር በማዋል አስፈላጊው ምርመራ እየተጣራበት መሆኑን የጉለሌ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ ገልጿል ።

ወንጀል ፈፃሚው በወቅቱ ከነ ኤግዚቢቱ በቁጥጥር ስር እንዲውል ህብረተሰቡ ከፖሊስ ጋር በመሆን አስፈላጊውን ትብብር ማድረጉ የሚያስመሰግን ተግባር ነው ያለው ፖሊስ ህዝብ ሲተባበር ወንጀል ፈጻሚዎችን በቀላሉ ለህግ ማቅረብ እንደሚቻልም አመላክቷል ብሏል።

የክፍለ ከተማው ፖሊስ ዋና መምሪያም ከአስተዳደሩ ጋር በመነጋገር የፍሳሽ መውረጃ ትቦ ውስጥ ገብተው ተጠርጣሪውን ለያዙት አባላት ማበረታቻና ሽልማት እንደሚሰጥም አሳውቋል።

አዲስ አበባ ፖሊስ

9 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.