(ዘ-ሐበሻ ዜና) "ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን" ሲሉ የምርጫ ቦርድ ሊቀመንበሯ ተናገሩ፡፡ የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ሊቀመንበር ወይዘሮ ሜላት ወርቅ ሀይሉ የምርጫውን ሂደት አስመልክተው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በምድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ለተፈጠረው ረጅም ሰልፍ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡ ችግሩ ሊፈጠር የቻለው በዲጂታል የተመዘገቡ መራጮች በርካታ በመሆናቸው የፊደል ቅደም ተከተል አሰራርና የካርድ ህትመት እጥረት በመፈጠሩ መሆኑን ጠቅሰው ካለዲጂታል የተመዘገቡ ግን ያለችግር እየተስተናገዱ እንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡
ሊቀመንበሯ ዛሬ ከጠዋቱ 12 ሰአት ጀምሮ 50,800 ምርጫ ጣቢያዎች ተከፍተው ምርጫውን ማካሄዳቸውን ገልፀው 695ቱ ደግሞ ዘግይተው መከፈታቸውን አስታውቀዋል፡፡ እንዲሁም በ143 ምርጫ ጣቢያዎች ደግሞ በፀጥታ ችግር የተነሳ ምርጫ ማካሄድ ሳይቻል መቅረቱን ገልፀዋል፡፡
እነዚህ ምርጫ ያልተካሄደባቸው ጣቢያዎች በአማራና በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ መሆናቸውን ያስታወቁት ሊቀመንበሯ ከእነዚህ መካከል ኩቻ፣ ሞኮሳና ቀርሳ እንደሚገኙበት ጠቅሰዋል፡፡ በዛሬው የምርጫ ሂደት አንድ የምርጫ ቦርድ አባል ህይወቱ ማለፉንም ወይዘሮ ሜላት ገልፀዋል፡፡ በነሞር ኢነር ምርጫ ክልል የምርጫ አስተባባሪ ሆነው የተመደቡት ግለሰብ በሞተር ሳይክል በደረሰባቸው አደጋ ህይወታቸው በማለፉ በምርጫ ቦርድ ስም የተሰማቸውን ሀዘን ገልፀዋል፡፡

3 days ago