ሰላም፤ እንደምን አደራችሁ?
7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ሊካሄድ አንድ ቀን ብቻ ቀርቶታል።
በነገው ዕለት የሚካሄደው 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድን ጨምሮ የጸጥታ ተቋማትና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገዋል፡፡
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የፀጥታና ደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል ምርጫው በስኬት እንዲከናወን ያደረገው ዝግጅት እጅግ ጠንካራ መሆኑን ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለምርጫው የሚያስፈልገውን የምርጫ ቁሳቁስ በሁሉም አካባቢዎች በፍጥነት ተደራሽ ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ለመሆኑ ከምርጫ ጋር ተያይዞ ችግሮች ሲፈጠሩ ዜጎች ማከናወን ያለባቸው ተግባራት የትኞቹ ናቸው ?
ምርጫ ቦርድ ዜጎች ከ7ኛው ጠቅላላ ምርጫ ጋር የተያያዙ ችግሮችንና ክስተቶችን ደኅንነቱ በተጠበቀና ፈጣን በሆነ መንገድ ጥቆማ የሚያደርጉበትን ከምርጫ ጋር ተያይዘው የሚፈጠሩ ችግሮች ሪፖርት ማድረጊያና ምላሽ መስጫ ሥርዓት ዘርግቷል።
በዚህም መሰረት ዜጎች ምን ምን ዓይነት ችግሮችን ጥቆማ ማድረግ ይችላሉ?
👉በምርጫ ሒደቶች ላይ የሚፈጠሩ መስተጓጎሎች፣
👉በድምፅ አሰጣጥ ወይም በቆጠራ ወቅት የሚያጋጥሙ ችግሮች፣
👉በምርጫ ጣቢያዎች አቅራቢያ የሚከሰቱ የፀጥታ ችግሮች፣
👉በመራጮች ላይ የሚደርስ ማስፈራራት ወይም ትንኮሳ፣
👉በምርጫ ቁሳቁስ ላይ የሚደርስ ጉዳት፣
👉ዐመፅ ወይም ዛቻዎች፣
👉ውጥረት የሚፈጥሩ የሐሰት መረጃዎች፣
👉እንዲሁም ምርጫውን ሊያስተጓጉል የሚችል ወይም ማንኛውም ሌላ አጠራጣሪ ድርጊት ጥቆማ ማድረግ ይችላሉ።
መቼ ጥቆማ መስጠትይኖርብዎታል?
👉የምርጫ ሒደቶች ሲስተጓጎሉ ሲመለከቱ፣
👉ከላይ የተጠቀሱትን ክስተቶች በቀጥታ ከተመለከቱ፣
👉የዐመፅ ወይም የግጭት ሥጋት ካለ፣
👉እንዲሁም አስቸኳይ ዕርምጃ የሚያስፈልጋቸው ማንኛውም ምርጫን የሚያውኩ ክስተቶች ከተመለከቱ።
እንዴት ጥቆማ መስጠት ይችላሉ? በሚከተሉት መንገዶች ጥቆማ መስጠት ይችላሉ፦
👉በነፃ የስልክ መስመር 6214 ላይ በመደወል
👉አጭር የጽሑፍ መልዕክት ወደ 7555 በመላክ
ሪፖርት ሲያደርጉ የሚከተሉትን መረጃዎች ለማካተት ይሞክሩ፦
👉ምን እንደተከሰተ ፣ የት እንደተከሰተ ፣ መቼ እንደተከሰተ ፣ ማን እንደተሣተፈበት (የሚታወቅ ከሆነ) ማን ጥቆማ መስጠት ይችላል?
የመገናኛ መንገዶች
👉ነፃ የስልክ መስመር 6214
👉አጭር የጽሑፍ መልዕክት 7555
👉አድራሻ: የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ| አዲስ አበባ
👉ድረ-ገጽ www.nebe.org.et

14 days ago