ከ6ሺ በላይ ለሚሆኑ የአዕምሮ ህሙማን ወደ ማህበረሰቡ እንዲቀላቀሉ የሚያግዝ ህክምና ተሰጠ
ይህ የህክምና ዓይነት በአእምሮ ጤና አውድ ውስጥ የተሃድሶ ህክምና የሚባል ሲሆን የአእምሮ ህመም ያለባቸው ሰዎች በህብረተሰቡ ውስጥ ሙሉ በሙሉ ተሳታፊ እንዲሆኑና ጥራት ያለው ሕይወት እንዲመሩ የሚረዳ የህክምና እና ድጋፍ ሂደት ነው።
በዚህም የአማኑኤል አዕምሮ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለ6ሺህ334 ዜጎች የተሀድሶ የህክምና አገልግሎት መስጠቱን የሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አብዩ የኔአለም ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።
ህክምናው ታካሚው የዕለት ከዕለት ተግባራቱን በራሱ እንዲያከናውን የሚረዳ ራስን መንከባከብ ፣ ንፅህናን መጠበቅ እና ከሰዎች ጋር እንዴት መግባባትና ጤናማ ግንኙነት መፍጠር እንደሚቻል የሚሰጥ ነው።
በተጨማሪም የስነልቦና እና ማህበራዊ ድጋፍ የሙያ እና ስራ ስልጠና እንዲሁም ከሆስፒታል የወጡ ታካሚዎች በቀጥታ ወደ ማህበረሰቡ ከመቀላቀላቸው በፊት የቅርብ ክትትል የሚደረግባቸው ጊዜያዊ ማቆያዎችን ማመቻቸትን ይጨምራል።
ታካሚው በተቻለ መጠን በሌሎች ላይ ጥገኝነቱ እንዲቀንስ ፣ያለ አድልዎና ማግለል በቤተሰብና በሰፈር ውስጥ እንዲይኖር የሚያስችል ሲሆን ህመሙ ተመልሶ እንዳይቀሰቀስ ራሱን እንዲጠብቅ ይረዳል ሲሉ አቶ አብዩ የኔአለም ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል።
Seledadotio

8 days ago