Logo
SeledaPost
በኢትዮጵያ የጉበት ካንሰር በሽታ ተጠቂዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተነገረ
 
የጉበት በሽታ ተጠቂዎች በወቅቱ ተገቢዉን የህክምና ክትትል ካላደረጉ ለጉበት ካንሰር እንደሚጋለጡ ተገልጿል ።ስር የሰደደ የጉበት በሽታ ፣የአልኮል መጠጥን ማዘዉተር ፣ከዉፍረት ጋር ተያይዞ የሚመጣ የጉበት በሽታ እንዲሁም የነቀዙና የሻገቱ ምግቦችን መመገብ ለጉበት ካንሰር አጋላጭ ከሆኑ ምክንያቶች መካከል ዋነኞቹ መሆናቸዉን በሀላባ ዞን የቁሊቶ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር እና የዉስጥ ደዌ ህክምና ስፔሻሊስት ዶክተር አብዱልቃድር መሀመድ ከብስራት ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ ገልፀዋል ።
 
በዓለማችን ላይ በዓመት 1 ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች በበሽታዉ የሚጠቁ ሲሆን ከፍተኛ የሞት መጠን እንደሚመዘገብም ተገልጿል ። በኢትዮጵያ በርካታ የጉበት በሽታ ተጠቂዎች ያሉ ሲሆን በወቅቱ ተገቢዉን ህክምና ሳይገኙ ስር ከሰደደ በኃላ የሚመጡ በመሆናቸዉ የጉበት ካንስር ተጠቂዎች ቁጥር እያደገ መምጣቱን ዶክተር አብዱልቃድር ተናግረዋል ።
 
በሽታው ጉበትን ለይቶ የሚያጠቃ የካንሰር አይነት ሲሆን ጉበት ላይ እባጭ በመፍጠር አገልግሎት እንዳይሰጥ የሚያደርግ ነዉ ያሉት ስፔሻሊስቱ ወደ ተለያዩ የሰዉነት ክፍሎች በመሰራጨት ለሞት የሚዳርግ የካንሰር አይነት መሆኑን አስረድተዋል ።
 
ከመጠን ያለፈ ድካም ፣ሆድ አካባቢ የሰዉነት እብጠት ፣ዓይን ወደ ቢጫነት መቀየር ፣የምግብ ፍላጎት መቀነስ ፣ማቅለሽለሽ እና ትዉከት ምልክቶቹ ሲሆኑ አብዛኞቹ ተጠቂዎች ምንም ምልክት ላያሳዩ ሰለሚችሉ በየጊዜዉ ምርመራዎችን ማድረግ አስፈላጊ ነዉ ተብሏል ።
 
በመባ ወርቅነህ

Seledadotio
Seledadotio
19 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.