የወለደችውን ህፃን ልጅ መፀዳጃ ቤት ለመክተት ስትታገል የነበረች እናት በእስራት ተቀጣች
በቦረና ዞን ዲሎቲ ወረዳ ውስጥ የወለደችውን ልጅ መፀዳጃ ውስጥ ለመክተት የሞከረችው ግለሰብ በእስራት ተቀጣች ።የቦረና ዞን ፖሊስ ዋና መምርያ የሴቶች እና ህጻናት ጉዳዮች ፅ/ቤት ሃላፊ ኮማንደር ወጋዬ ዲዶ ለብስራት ሬዲዮ እንገለጹት ተከሳሽ መገርቱ ጋሹ የተባለች ተከሳሽ ሚያዝያ 5 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ ስምንት ሰዓት ላይ ሴት ልጅ በሰላም መገላገሏ ተገልጿል ።
ተከሳሿ በሰላም የወለደቻትን ሴት ልጅ ለተወሰኑ ቀናት አጠገቧ ካቆየቻት በኋላ ማንም ሳያያት መፀዳጃ ቤት በመግባት ህጻኗን ጉድጓድ ውስጥ በጭንቅላቷ ለመክተት ስትሞክር የህጻኗን ለቅሶ የሰሙት ሰዎች ህጻኗን ከሞት ማትረፋቸው ተገልጿል። ድርጊቱን ስትፈጽም የነበረችው ተከሳሽ በቁጥጥር ስር ውላለች።ፖሊስም ህጻኗን ወዲያው ለህክምና ወደ ጤና ተቋም በመላክ ተከሳሿ ላይ በበቂ ማስረጃ የምርመራ መዝገቡን በማጣራት ለአቃቢ ህግ አስተላልፏል። አቃቢ ህግም ከፖሊስ የተላከውን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በተከሳሿ ላይ በህጻን ልጅ መግደል ወንጀል ሙከራ ክስ የመሰረተባት እንደሆነ ገልፀዋል።
በአቃቢ ህግ የተመሰረተውን ክስ የተመለከተው የቦረና ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም በዋለ ችሎት ተከሳሽ መገርቱ ጋሻው አስባና አቅዳ የወለደቻትን ልጅ ለመግደል በመፀዳጃ ቤት ለመክተት ስትሞክር በመያዟ በአምስት አመት ፅኑ እስራት እንድትቀጣ የተወሰነባት መሆኑን ኮማንደር ወጋዬ ዲዶ ጨምረው ለብስራት ሬዲዮ ገልፀዋል። ህጻኗ በተደረጋላት የተፋጠነ የህክምና እርዳታ በሙሉ ጤንነት ላይ እንደምትገኝና ወደፊት ህጉን በጠበቀ መሰረት ለአሳዳጊ እንደምትሰጥ ገልፀዋል።via_dagu
Seledadotio

25 days ago