Logo
SeledaPost
የታሸጉ ምርቶች ተጠቃሚነት በመጨመሩ ታዳጊዎችን ለደምግፊት እየተጋለጡ ይገኛል

እንደ ግፊት ያሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ከዕድሜ ጋር ቁርኝት ያላቸዉ ሲሆን ዕድሜ በጨመረ ቁጥር የመከሰት ዕድላቸዉ ሰፊ ነዉ። ነገር ግን ታዳጊዎች ለዚህ ችግር ተጋላጭ እየሆኑ መምጣታቸዉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል ።

በሚኒስቴሩ የበሽታዎች መከላከልና መቆጣጠር መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ህይወት ሰለሞን ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ከ50 በመቶ በላይ የማህበረሰብ የሞት ምክንያት እየሆኑ መምጣታቸውን ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል ።

የአኗኗር ስርዓት እየተቀየረ መምጣት በተለይ በፋብሪካ ዉስጥ ተቀነባብረዉ የሚያልፉ ምግቦችን አዘዉትሮ መጠቀም የታዳጊዎችን ለግፊት ተጋላጭነት እየጨመረ ይገኛል ። በፋብሪካ ተቀነባብረዉ የሚያልፋ ምግቦች ለጤና ጠቃሚ ያልሆኑ ይዘት ያላቸዉ በመሆኑ ለበሽታው አጋላጭ ናቸዉ።

ከእነዚህም መካከል ከፍተኛ የጨዉ መጠን ያላቸዉ የታሸጉ ምግቦች በስፋት በህፃናትም ይሁን በአዋቂዎች ዘንድ ተመራጭ እየሆኑ መምጣታቸዉን ያነሱት ዶክተር ህይወት በተመሳሳይ መልኩ የቅባት አይነታቸዉ ለጤና ጠንቅ የሆኑ ምግቦች በስፋት ጥቅም ላይ ሲዉሉ ይስተዋሏል።

በተጨማሪም በመጠጥ ይሁን በደረቅ ምግብ ላይ የስኳር መጠናቸው ከፍተኛ የሆኑ ምግቦች ተመራጭ እየሆኑ መጥተዋል ። ሌሎች አጋላጭ ምክንያቶች እንዳሉ ሆነዉ ታዳጊዎች ላይ የሚከሰት የደም ግፊትን ለመከላከል የታሸጉ ምርቶች አጠቃቀምን ማስተካከል ይገባል። ልጆቻቸዉን የለስላሳ መጠጦችንና የታሸጉ ምርቶችን አሲዘዉ ትምህርት ቤት የሚልኩ ወላጆች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ጥሪ ተላልፋል።

1.4 ቢሊዮን የሚሆነዉ የዓለም ህዝብ ከፍተኛ ከሆነ የደም ግፊት ጋር እንደሚኖር የጤና ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል።

Seledadotio
Seledadotio
20 days ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.